ዳንኤል አንድሩስ ለዘጠኝ ዓመትታ ቪክቶሪያን በ48ኛ ፕሪሚየርነት ማገልገል ታላቅ ክብር መሆኑን ገልጠው፤ የማልግሬቭ ምክር አባልነታቸውንም አክለው በፈቃዳቸው እንደሚለቅቁ ያስታወቁት ዛሬ ማክሰኞ ከቀትር በኋላ ነው።
ሁሌም "በቀላሉ ዝነኛ የሚያደርግ ላይ ሳይሆን፤ ሁሌም ትክክለኛ ለሆነ ተግባር በብርቱ መሥራት" ላይ አተኳሪ እንደነበሩ የገለጡት ፕሪሚየር አያይዘውም " የመሰናበቻውና ይህን ልዩና አስደማሚ ኃላፊነት ለሌላ ተረኛ አሳልፎ የመስጫው ጊዜ አሁን ነው" ሲሉ የስንብት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ዳንኤል አንድሩስን በፕሪሚየርነት የሚተኩት መሪ ነገ ከቀትር በኋላ በሌበር ፓርቲ ተመርጠው ኃላፊነቱን ይረከባሉ።
ዳንኤል አንድሩስ 48ኛው የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ሆነው የተመረጡት ኖቬምበር 2014 ሲሆን በ2018 እና 2022 ለሶስት ጊዜያት በአብላጫ ድምፅ በቪክቶሪያ ነዋሪዎች ተመርጠዋል።