የአንጋፋው የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃ አቀንቃኝ ዘሪሁን ወዳጆ የቀብር ሰነ-ስረዓት በመንበር ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴደራል ቤተክርስቲያን የፌደራልና የክልል ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ዘመድ ወዳጆቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት ተፈፀሟል።
አርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ በምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ በ1949 ዓ.ም የተወለደ ሲሆን ለ48 ዓመታት በአፋን ኦሮሞ የተለያዩ ይዘት ያላቸው ሙዚቃዎች በማቀንቀን ትልቅ አስተዋጽኦ ሲያደረግ ቆይቷል።
አርቲስቱ ባጋጠመው ሕመም ምክንያት በሕንድ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ከቀናት በፊት ህይወቱ ማለፉ የሚታወስ ነዉ፡፡