በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት 896,520 ተማሪዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ ያመጡት 29,909 ብቻ ናቸው ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ

በክልል ደረጃ ይኼ ነው የሚባል የውጤት ልዩነት እንደሌለ የተገለፀ ሲሆን አዲስ አበባ፣ሐረሪ እና ድሬደዋ የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል።

Students of Asfaw Wossen High School .jpg

Students of Asfaw Wossen High School in Addis Ababa, Ethiopia, on February 2, 2021. Credit: Minasse Wondimu Hailu/Anadolu Agency via Getty Images

የትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት ዋና ዋና ግኝቶችን ይፋ አድርጓል።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2014 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች በአዲስ መልክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርስቲዎች መሰጠቱን አስታውሰው፤ይህ አዲስ አካሄድ ቀጣይ እርምጃዎቻችንን የሚለኩ ነበሩ ብለዋል።

ሀቀኛ እና ትክክለኛ የተማሪዎችን የትምህርት ክህሎት በመለካት የፈተና ሂደቱ ከኩረጃ፣ የፈተና ስርቆት የፀዳ እንደሆነና በዚህ ፈተና ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ የሚኮሩበት ነው ተብሏል።

በ2014 ዓም የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985ሺ 3354 ተማሪዎች ሲሆኑ ለፈተና የቀረቡት 92.2 % 908ሺ ሺህ 256 ተማሪዎቹ ሲሆኑ 77ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አንዳልወሰዱ ተመልክቷል።

በደንብ ጥሰት ፣ለመኮራረጅ በመፈለግ እና በሌሎች ምክንያቶች 50ሺህ 170 ተማሪዎች ሳይፈተኑ ቀርተዋል።

በ2014 የትምህርት ዘመን 899ሺህ 520 ተማሪዎች ተፈትነዋል ።

በፆታ ማዕከልነት የአማካይ ውጤት በወንዶች 30.2 እንዲሁም ሴቶች 28.09 % አማካይ ውጤት አስመዝግበዋል።

በትምህርት ዘርፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ በተሻለ ውጤት ያስመዘገቢ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ 31.63 ከመቶ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ 27.79 ከመቶ በአማካኝ አስመዝግበዋል።

በክልል ደረጃ ይኼ ነው የሚባል የውጤት ልዩነት እንደሌለ የተገለፀ ሲሆን አዲስ አበባ፣ሐረሪ እና ድሬደዋ የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል።

ከተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወንድ ከ 700፤ 666 ያስመዘገበ ሲሆን 650 ሴት ተማሪ አስመዝግባለች።በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ወንድ 524 አስመዝግቧል።እነዚህ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎይ በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና እና ሽልማት ይሰጣቸዋል ተብሏል።

Share

Published

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service