የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በገዛ ፈቀዳቸው ከኃላፊነት ለመልቀቅ በመወሰን መልቀቂያ ማቅረባቸውን አሳወቁ።
ብርቱካን ሚደቅሳ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት ከኃላፊነት ለመልቀቅ የወሰኑት በጤና ችግር ምክንያት ነው።
" ጤናዬን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልገኝ ሆኖ በመገኘቱ ከነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቦርድ ሰብሳቢነቴ በገዛ ፍቃዴ መልቀቄን ለተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ጽሕፈት ቤት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሳውቄያለሁ " ብለዋል።
በሚቀራቸው ጊዜ ያልተጠናቀቁ ስራዎችን የማጠናቀቅ እና አስተዳደራዊ ሽግግር የመፈፀም ሃላፊነቶችን እንደሚወጡም አስታውቀዋል።