የአውስትራሊያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ሶኮሩስ ቱኒዚያን 1 ለ 0 ማሸነፍ አውስትራሊያ ውስጥ "ግዙፍ ድል" ተብሎለታል።
አውስትራሊያን ለአሸናፊነት ያበቃችውን ግብ በ23ኛው ደቂቃ ያስቆተረው ዱክ ስተላር ነው። ይህም አውስትራሊያን ለሚቀጥለው የጥሎ ማለፍ ደረጃ ሊያደርስ ይችላል የሚል ተስፋ አሳድሯል።
አውስትራሊያ ቀደም ባለው የመጀመሪያ ግጥሚያዋ በፈረንሳይ 4 ለ1 ተሸንፋለች።
ግቧን ያስቆጠረው ስቲላር "ቃላቶች የሉኝም። ትልቅ ሁነት ነው። ለቅሶ እየከጀለኝ ነው"
"አሁን በስሜት መዋጥ አልሻም። ከዴንማርክ ጋር አንድ ቀሪ ሥራ አለን። ጊዜው ለዋስትራሊያ ተጨማሪ ታሪክ መሥሪያ ነው" ሲል ከግጥሚያው በኋላ ለ SBS ገልጧል።