"የፒያኖዋ እመቤት" እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ አረፉ

በኢትዮጵያ ቀዳሚዋ የቫዮሊን እና ፒያኖ አቀናባሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው “የፒያኖዋ እመቤት” እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ በ99 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

Emahoy Tsegie Mariam.jpg

Emahoy Tsegie Mariam. Credit: PR

እማሆይ ፅጌማርያም ከአባታቸው ገብሩ ደስታ እና እናታቸው ካሣዬ የለምቱ በ1916 በአዲስ አበባ ውስጥ የተወለዱ ሲሆን፤ በልጅነታቸው ለትምህርት በሄዱባት ስዊዘርላንድ ፒያኖን በደንብ ተምረዋል።

ከትምህርት መልስም በ19 ዓመታቸው ወደ ወሎ ግሸን ማርያም ገዳም በመሄድ በ21 ዓመታቸው ምንኩስናን ተቀብለዋል።

ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ስም የውብዳር ሲሆን፤ በወጣትነታቸው ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ መጠሪያቸው ወደ እማሆይ ፅጌማርያም ተቀይሯል።

ከ1984 ጀምሮ ኑሯቸውን በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ "ቅድስቲቷ ከተማ" ተብላ በምትጠራው እየሩሳሌም አድርገዋል።

አባታቸው ገብሩ ደስታ የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩ ሲሆን፤ በአፄ ሃይለስላሴ ዘመንም የፓርላማ አፈ ጉባኤ በመሆን ማገልገላቸውን የቤተሰባቸው ታሪክ ያስረዳል።

እማሆይ ፅጌ ማርያም እንግሊዝኛ፣ ጀርመንኛ፣ ዕብራይስጥኛ፣ አማርኛና ግዕዝን አቀላጥፈው የሚናገሩ ሲሆን፤ የተለያዩ የሙዚቃ ሥራዎቻቸው በማቅረብ የሚገኙትንም ገንዘብ ለድሆች መርጃ አውለዋል።

እማሆይ ፅጌማርያም ከሰሯቸው ከበርካታ የሙዚቃ ሥራዎች ውስጥ « Homeless Wonder » ፣ « The Son of Seam »፣ « The Mad Man's Daughter » እና « Mother's Love » የሚል አርዕስት ያላቸው ሙዚቃዎች እንደ ምሳሌ ይጠቀሳሉ።

እማሆይ ፅጌማርያም በሙዚቃ መሳርያ ብቻ የተቀናበሩ ረቂቅ ሙዚቃ በመጫወት በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያዋ ሴት መሆናቸውም ይነገርላቸዋል።

Share

Published

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service