የፌዴራል በጅሮንድ ጆሽ ፍራይደንበርግ የ2022/23 በጀት ዛሬ ማምሻውን በፓርላማ ተገኝተው ይፋ አድረገዋል።
በዚህ መሠረት፤
- ለ10 ሚሊየን ዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ገለሰቦች ከዚህ ዓመት ጁላይ 1 ጀምሮ የእንድ ጊዜ 1,500 ዶላርስ፣ ጥንዶች 3,000 የግብር ቅናሽ ያገኛሉ።
- ለጡረተኞችና የቅናሽ ካርድ ተጠቃሚዎች $250 የአንድ ጊዜ የጥሬ ገንዘብ ክፍያ፤ በጥቅሉ $5.6 ቢሊየን ወጪን ያስከትላሉ።
- የነዳጅ ቀረጥ ለስድሰት ወራት አሁን ካለው በሊትር 44 ሳንቲም በግማሽ ይቀንሳል። በአንድ ታንከር $15 ቁጠባ ያስገኛል፤ በጥቅሉ $3 ቢሊየን ወጪን ያስከትላል።
- ጠቅላላ የአገሪቱ ዕዳ በ2023-24 ከአንድ ትሪሊየን ዶላር በላይ ያሻቅባል፤ በ2025-26 ወደ $1.17 ትሪሊየን ዶላር ወይም 44.7% ጠቅላላ የአገር ውስጥ ይንራል።
- የሙዋዕለ ንዋይ ፍሰት ጉድለት በ2021-22 እስከ $79.8 ቢሊየን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
- በቀጣይ አራት ዓመታት ውስጥ $224.7 ቢሊየን ሊደርስ ይችላል።
- ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት 4.25% በ 2021-22, 3.5% በ 2022-23 እና 2.5% በ 2023-24 ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል።
- የአውስትራሊያ ሥራ አጥነት መጠን በዚህ ዓመት የሴፕቴምበር ፋይናንስ ሩብ ዓመት ወደ 3.75% ዝቅ ይላል ተብሎ ይታሰባል።
- ለሜዲኬይር ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት 133 ቢሊየን ዶላርስ በጀት ውስጥ ገብቷል።
- 18 ሚሊየን ዶላርስ ለመድብለባህል ማሕበረሰባት የአዕምሮ ጤና ድጎማ ተመድቧል።
- ለመከላከያ ለአሥር ዓመታት 270 ቢሊየን ዶላርስ ተበጅቷል።