የምዕራብ አውስትራሊያ ፕሪሚየር ማርክ ማጋዋን በድንገት ከኃላፊነታቸው መልቀቅ ያልተጠበቀ አስደንጋጭ ዜና ሆኗል።
ማክጋዋን፤ ከማርች 2017 አንስቶ ፕሪሚየር ሆነው ምዕራብ አውስትራሊያን መርተዋል፣ በኮቪድ 19 ወረርሽ ቀውስ ወቅት አመራር ሰጥተዋል፣ በ2021 በመጠነ ሰፊ የምርጫ ውጤት ለአሸናፊነት በቅተዋል።
ባለፈው ማርች በሕዝብ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት 63 ፐርሰንት ነበር።
ፕሪሚየር ማርክ ማክጋዋን ለምን ኃላፊነታቸው ለመልቀቅ እንዳሹ ሲገልጡ፤
"እንደዋዛ የወሰንኩት ውሳኔ ሳይሆን፤ እውነቱ እጅግ በጣም መድከሜ ነው። በእጅጉ ደክሞኛል" ብለዋል