በተጫዋችነቱ ዘመን "የእግር ኳስ ንጉሥ" ተብሎ ይወደስ የነበረው የ82 ዓመቱ ፔሌ ለሕልፈተ ሕይወት የበቃው በሳኦ ፓውሎ አልበርት አንሽታይን ሆስፒታል እያገገመ ይገኝበት በነበረው ሆስፒታል ነው።
የካንሰር ሕመም ተጠቂው ፔሌ ላለፉት ጥቂት ሳምንታት የመተንፈሻ አካል ሕክምና እንደተደረገለትና በማገገምም ላይ ይገኝ ነበር።
ኤድሰን ኤራንተስ ዶ ናሲመንቶ ወይም በፖርቹጋል አጠራር "ፔሌ" በኢትዮጵያውያን ዘንድ በእጅጉ ተወዳጅና ዝናው የገነና በፊፋም "የ20ኛው ክፍለ ዘመን ታላቁ የእግር ኳስ ተጫዋች" ተብሎ የተሰየመ ነው።
በእግር ኳስ ተጫዋችነት ዘመኑ ከተጫወታቸው 1,363 ግጥሚያዎች 1,279 ግቦችን በማስቆጠር የዓለም ሬኮርድ ባለቤት ሆኗል።

Picture shows a statue of Brazilian football legend Pele in Doha on December 6, 2022, during the Qatar 2022 World Cup football tournament. Credit: ANDREJ ISAKOVIC / AFP) (Photo by ANDREJ ISAKOVIC/AFP via Getty Images)
የፔሌን ሕልፈተ ሕይወት ተከትሎ ከአገር መሪዎች እስከ እግር ኳስ አድናቂዎች የተለያዩ የሐዘን መግለጫዎች እየጎረፉ ነው።