ከዋናው የበዓሉ ቀን አስቀድሞ በነበሩት ቀናትም የቁንጅና ውድድር፣ ሩጫ፣ የቅኔ ምሽትና ሌሎችም ሁነቶች ተካሂደዋል።
የሀገር ውስጥና የውጪ ጎብኚዎች እንዲሁም የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች በዓሉን እየታደሙ ይገኛሉ።
የአገው ፈረሰኞች በዓል በጣልያን ወረራ ወቅት ፈረሰኞች የፈፀሙትን ተጋድሎ ለመዘከር ከ83 ዓመታት በፊት የተመሰረተ ነው።
ማህበሩ አሁን ላይ ከ62 ሺህ በላይ አባላት ያሉት ሲሆን፤ የማህበሩ አባላት እርስ በርስ እንዲረዳዱ እና ማህበራዊ ጉዳዮችን በጋራ እንዲከውኑ እድል ፈጥሯል።
የአገውን ሕዝብ ባሕልና ማንነት በማስተዋወቅ ረገድም ማህበሩ የጎላ ሚና እየተጫወተ መሆኑ በበዓሉ ላይ ተገልጿል።