በዛሬው ምሽት ሜልበርን በተካሔደው የምድብ ግጥሚያ አውስትራሊያ ካናዳን ረትታ ለትሎ ማለፍ ዋንጫ ውድድር አልፋለች።
አውስትራሊያ ከግማሽ ፍፃሜ በፊት ሁለት ግቦቿን በሃይሊ ራሶ አማካይነት በ9ኛ እና 39ኛ ደቂቃዎች አስቆጥራለች።

MELBOURNE, AUSTRALIA - JULY 31: Mary Fowler of Australia in action during the FIFA Women's World Cup Australia & New Zealand 2023 Group B match between Canada and Australia at Melbourne Rectangular Stadium on July 31, 2023, in Melbourne, Australia. Credit: Cameron Spencer/Getty Images
ከዕረፍት በኋላ በተካሔደው ግማሽ ጨዋታ አውስትራሊያ ሶስተኛ ግቧን በሜሪ ፎውለር አማካይነት በ58ኛዋ ደቂቃ እንዲሁም 4ኛ የድል ግብ በስቴፋኒ ካትሊ ከመደበኛ 90 ደቂቃ ተጨማሪ ሰዓት በ94ኛ ደቂቃ ለማስቆጠር ችላለች።

Canada's goalkeeper #01 Kailen Sheridan (L) concedes a goal scored by Australia's forward #16 Hayley Raso during the Australia and New Zealand 2023 Women's World Cup Group B football match between Canada and Australia at Melbourne Rectangular Stadium, also known as AAMI Park, in Melbourne on July 31, 2023. Credit: WILLIAM WEST/AFP via Getty Images
በተመሳሳይ ሰዓት ናይጄሪያና አየርላንድ ማምሻውን ባካሔዱት ግጥሚያ 0 ለ 0 ተለያይተዋል።
ቀደም ሲልም በዛሬው ዕለት በተካሔዱ ግጥሚያዎች ጃፓን ስፔይንን 4 ለ ዜሮ፣ ዛምቢያ ኮስታ ሪካን 3 ለ 1 አሸንፈዋል።
በነገው ዕለት ቬትናም ከኔዘርላንድስ፣ ፖርቱጋል ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ቻይና ከእንግሊዝ እና ሃይቲ ከዴንማርክ ጋር ይጋጠማሉ።