አንቶኒ አልባኒዚ 31ኛው የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ዛሬ ሰኞ ከቀትር በፊት ቃለ መሃላ ፈጸሙ።
አዲሱ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቃለ መሃላቸውን ከፈፀሙ በኋላ እምብዛም ሳይቆዩ ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ጃፓንና ሕንድ መሪዎች ጋር ቶኪዮ ላይ ለሚታደሙበት ስብሰባ አቅንተዋል።
አቶ አልባኒዚ የሽግግር ሚኒስቴር ለማቆም ቃለ መሃላቸውን የፈፀሙት ካንብራ ከሚገኘው ቤተ መንግሥት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሪቻርድ ማርልስ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ፣ በጅሮንድ ጂም ቻልመርስና የፋይናንስ ሚኒስትር ካቲ ጋለኸር ጋር በመሆን ነው።

Anthony Albanese stands in front of The Governor-General, His Excellency General the Honourable David Hurley AC DSC (Retd) on May 23, 2022 in Canberra. Source: Getty
ዛሬ ቃለ መሃላ የፈፀሙት ሚኒስትሮች ሙሉ የምርጫ ውጤት ይፋ እስኪሆን ድረስ የሌሎች ሚኒስትሮችን የሥራ ኃላፊነት ደርበው ይሠራሉ።
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ትናንት እሑድ ምሽት ባወጡት መግለጫ የስብሰባውን አጋጣሚ በመጠቀም የአየር ንብረት ለውጥና ሪጂን ተኮተር ጠንካራ የውጭ ፖሊሲ አጀንዳ ግብር ላይ ለማዋልም እንደሚጠቀሙበት ገልጠዋል።
አክለውም፤ የአራትዮሹ የመሪዎች ስብሰባ አራት ሊብራል ዲሞክራሲ አገራትን አንድ ላይ እንደሚያመጣ፣ ለኢንዶ ፓስፊክ ድጋፍ እንደሚሰጥና የደቡባዊ ምስራቅ እስያ አገራትን ማዕከል እንደሚያደርግ፣ መንግሥታቸውም በጤና፣ ፀጥታና የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ከአርትዮሹ አገራት ግንኙነት በኩል ተባብሮ እንደሚሰራ አመላክተዋል።
ፕሬዚደንት ባይደን አቶ አልባኒዚ ወደ ቶኪዮ ከማቅናታቸው በፊት ትናንት እሑድ ስልክ ደውለው አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ማነጋገራቸውን አስታውቀዋል።
አቶ አልባኒዚ ረቡዕ ከቶኪዮ ወደ አውስትራሊያ ይመለሳሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጃፓናውያን የአራትዮሹን ስብሰባ በመቃወም ቶኪዮ ላይ ሰልፍ ወጥተዋል።
የተወሰኑ የተቃውሞ ሰልፈኞች በጎዳናዎች ላይ ሲተምሙ ሌሎች እግሮቻቸውን አጣጥፈው "ጦርነት አያሻም" እና "ጦርነቶችን ተቃመውሙ፤ ጦርነት ለበስ ስብሰባዎችን ክሉ" የሚሉ ነፈክሮች የተፃፉባቸው ደማቅ ቢጫ ሰደርያ ለብሰው ተገኝተዋል።
ከተቃውሞ ሰልፈኞቹ አንዱ የሆነው ኦታ "በዩናይትድ ስቴትስ የሚመራሩት የምዕራብ አውሮፓ አገራትና የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን አባላት ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ለዩክሬን በማቀበል በሩስያና ዩክሬይን መካክል ግጭቶችን አባብሰዋል፣ ዕቅውባዎችን በሩስያ ላይ ጥለዋል። እኒህ ሁሉ ግጭትን አይገቱም፤ ከማባባስና እንዲራዘም ከማድረግ በስተቀር። እንዲህ ያሉ ድርጊቶችን ይቅር አልልም" ብሏል።