በሊዮኔል ሜሲ አምበልነት የተመራውና በ1978 እና በ1986 ለሁለት ጊዜያት የዓለም ዋንጫ ባለቤት የሆነው የአርጀንቲና ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን በዛሬው ዕለት በሳዑዲ አረቢያ ኳታር ላይ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረቷል።
ግቦቹን ያስቆጠሩት በአርጀንቲና በኩል በ10ኛው ደቂቃ ሊዮኔል ሜሲ ሲሆን፤ በሳዑዲ አረቢያ በኩል በ48ኛው ደቂቃ ሳሌህ አል - ሺህሪና በ53ኛው ደቂቃ ሳሌም አል-ዳውሳሪ ናቸው።
ለዋንጫ ተፋላሚ ሊሆን ይችላል ተብሎ የተገመተው የደቡብ አሜሪካ ቡድን በመካከለኛው ምሥራቅ ቡድን መረታት በመላው ዓለም የስፖርት ተቺዎች ዘንድ ግርምታን አስከትሏል።
አርጀንቲና ቀደም ሲል ሳዑዲ አረቢያን ሁለት ጊዜ ያሸነፈችና ሁለቴ አቻ የወጣች ሲሆን፤ ይህ የመጀመሪያ ሽንፈቷ ነው።