ደራሲ፣ አዘጋጅና ተዋናይት ባዩሽ አለማየሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

*** ባዩሽ ዓለማየሁ የታዋቂው ተርጓሚና ደራሲ መስፍን ዓለማየሁ ልጅ ናት።

Bayush Alemayehu

Bayush Alemayehu Source: Supplied

ባዩሽ ዓለማየሁ በአገር ፍቅር ቴአትር ቤት በተዋናይትነት ለረጅም አመታት አገልግላለች።

በርካታ አጫጭር ተከታታይ ድራማዎችን፣ ትረካዎችን፣ የመድረክ ትያትሮች ላይም በተዋናይነት እንዲሁም በአዘጋጅነት ስትሰራ ቆይታለች፡፡

ደራሲ፣ አዘጋጅና ተዋናይት ባዩሽ ዓለማየሁ እጅግ ጥቂት ከሚባሉ ሴት ፀሃፌ ተውኔቶችና አዘጋጆች ተርታ የምትመደብ ሲሆን በአገር ፍቅር ቴአትር ቤት በተዋናይትነት ለረጅም ዓመታት አገልግላለች።

ብዙዎች በመድረክ አተዋወኗ ብቃቷ የምትደነቀው ባዩሽ

- የቬኑሱ ነጋዴ

- የስለት ልጅ

- ሰማያዊ አይን ትዳር ሲታጠን

- ሰዓት ዕላፊ

- ነቃሽ ...በትወና የተሳተፈችባቸው ተውኔቶች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው።

ረመጥ እና ፎርፌ እንዲሁም ገፅ ሁለት የተሰኙ ተውኔቶችንም ደርሳለች።

ባዩሽ ገጣሚና ተራኪም ጭምር የነበረች ሲሆን ፓፒዮ የተሰኘውን ረጅም ልብ ወለድ ድርሰት እና ሌሎችንም ስራዎች በሬዲዮ ፋና ተርካለች።

ባዩሽ ዓለማየሁ የታዋቂው ተርጓሚና ደራሲ መስፍን ዓለማየሁ ልጅ ናት።

በሕመም አልጋ እስከምትይዝበት ዕለት ድረስ በአገር ፍቅር ቴአትር ቤት በድጋሚ ሊታይ በነበረው ሰዓት ዕላፊ በተሰኘው የቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ተውኔት ላይ በልምምድ ላይ ነበረች ተብሏል።

አርቲስቷ ባጋጠማት ህመም ምክንያት በህክምና ስትረዳ ቆይታ ነው ትናንት ታህሳስ 23/2013 ዓም ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በህክምና ስትረዳ በቆየችበት በየካቲት 12 ሆስፒታል ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።


Share

Published

By Stringer Report

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
ደራሲ፣ አዘጋጅና ተዋናይት ባዩሽ አለማየሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች | SBS Amharic