በአውስትራሊያ የቻይና አምባሳደር ሺያኦ ችየን የአውስትራሊያ በታይዋን ጉዳይ ጣልቃ መግባት ከወዲሁ ውጥረት ግብቶት ያለውን የአውስትራሊያ - ቻይና ግንኙነት ይበልጡን ሊጎዳ እንደሚችል አሳሰቡ።
አምባሳደሩ ይህን ያሉት በዛሬው ዕለት በአውስትራሊያ ብሔራዊ ፕሬስ ክለብ ተገኝተው ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው።
ቻይና የዩናይትድ ስቴትስ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲን የታይዋን ጉብኝት ተከትሎ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በታይዋን ባሕረ ሰላጤ ያካሔደች ሲሆን፤ የወታደራዊ ሚሳይል ውንጨፋዎቿም የአካባቢውን ሰላምና መረጋጋት ለውጥረት ዳርጓል።
በቤጂንግ ዕይታ ግና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎቿ ለአፈ ጉባኤዋ ያልተወደደ ጉብኝት አግባብ ያለው ስለመሆኑ ተመልክቷል።
ይሁንና የቤጂንግ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች "ከመጠን ያለፈ አፀፋ" እና በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ላይ "ውጥረት" ፈጣሪ ነው በሚል በአውስትራሊያ በኩል በተቃራኒው ተገልጧል።
አምባሳደር ሺያኦ ግና የአውስትራሊያ የአፈ ጉባኤ ፔሎሲን የታይፔ ጉብኝት ደግፎ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ማበር ተገቢ አይደለም ሲሉ ተችተዋል።
አክለውም፤ የአውስትራሊያ መንግሥት የታይዋንን ጉዳይ 'በጥንቃቄ" እንዲይዝ አሳስበዋል። የቻይና አንድ አውራጃ በሆነቸው ደሴት ጉዳይ "ምንም ዓይነት የመቻቻል ሥፍራ አይኖርም" ሲሉም በከረረ ድምፀት ተናግረዋል።
ደሲቱትን ከእናት አገርዋ ጋር "ለማዋሃድ" ቻይና "ማናቸውንም አስፈላጊ እርምጃ ሁሉ" እንደምትወስድ በግልፅ አስቀምጠዋል።

China announced six exclusion zones around Taiwan for military drills after the visit of US House Speaker Nancy Pelosi. Credit: SBS News
አያይዘውም፤ የአውስትራሊያ መንግሥት በ'አንድ ቻይና ፖሊሲ' ረግቶ እንዲቀጥል ዳግም አሳስበዋል።
ንፅፅራዊ ምሳሌነቱ መልካምነት እንደሚጎድለው አመላክተውም "ታዝማኒያ የአውስትራሊያ አካል ትሆናለች፣ ነበረችም፤ ናትም" ብለዋል።