ባለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል በፍርድ ቤቶች ላይ የአሰራር ማሻሻያ ቢደረግም፤ የሚፈለገው ለውጥ አለመምጣቱን የሕግ ባለሙያዎች ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት የሕግ የበላይነትና በፍትህ አካላት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው፡፡
በምክክሩ ላይ አገሪቷ ለውጥ ውስጥ ከገባች ጊዜ ጀምሮ በሕግ የበላይነትና በፍትህ ዘርፍ ላይ የተከናወኑ ሥራዎች ሕዝብ በሚፈልገው ደረጃ ላይ አለመሆናቸው ተገልጿል፡፡
በተለይ ፍርድ ቤቶች ላይ የነበረው የተንዛዛና በሙስና የተሳሰረ አሰራር ተባብሶ መቀጠሉን ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ የፍትህ አካላትን አለመጠናከራቸውንም አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸዋል፡፡
የሚመለከታቸው አካላትየፍትህ ዘርፍ ሰብዓዊና ለዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ባለው ድርሻ ቅድሚያ እንዲሰጡትም ተጠቁሟል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ከባለሙያዎቹ የሚያገኛቸውን ግብዓቶች ዘርፉን ለማሻሻል በሚደረጉ ጥናቶች እንደሚጠቀምባቸው ተመልክቷል፡፡
[ ኢዜአ ]