ቪክቶርያ ምንም አይነት የኮሮናቫይረስን ሳታሳይ 23 ቀናትን አስቆጥራለች፡፡
ይህንኑ ተከትለው የቪክቶርያ ፕሪምየር ዳንኤል አንድሪውስ ተጨማሪ ገደቦች መላላታቸውን ይፋ አድርገዋል
- 25 % የሚሆኑ እና በግል ድርጅቶች የሚሰሩ ከኖቬምበር 30 በኋላ ወደ ስራ ገበታቸው ይመላሳሉ
- በመኖሪያ ቤት ከሰኞ ጀምሮ እስከ15 ሰዎችን ማስተናገድ ይቻላል
- ከመኖሪያ ቤት ወጭ እስከ 50 ሰዎች በአንድ ላይ መሰባሰብ ይችላሉ
- የፊት መሸፈኛ በሁሉም ቦታ ግዴታነቱ ቀርቶ ቦታ እየተመረጠ የሚደረግ ይሆናል
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሜልበርን ከንቲባ ሳሊ ካፕ ከተማዋ የሜልበርን ነዋሪዎች እና በከተማ አካባቢ የሚሰሩ ሰራተኞችን በደስታ ለመቀበል መዘጋጀቷን አስታውቀዋል ፡፡