የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ የአየር ሰአት ድልድል መመሪያ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሚዲያዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይቱ የአየር ሰአት ድልድል ቀመር፣ ድልድሉ ከዚህ በፊት የተካሄደበት መንገድ እና የድልድሉ ማከናወኛ ቴክኖሎጂ በቦርዱ እና በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አማካኝነት እንደቀረቡም ቦርዱ አስታውቋል።
በውይይቱም ከዚህ ቀደም በፓርላማ መቀመጫ ያለው ፓርቲ የሚያገኘው የአየር ሰአት ከ60 በመቶ ወደ 5 በመቶ እንዲቀንስ መደረጉ የውድድሩን ሜዳ የተሻለ እንደሚያደርገው የፓርቲዎች ተወካዮች ገልጸዋል ብሏል ቦርዱ፡፡
ለአየር ሰአት ድልድሉ ከፓርላማ መቀመጫ መስፈርት በተጨማሪ፡
- በእኩል የሚደለደል 25 በመቶ
- ፓርቲው በሚወዳደርበት የፌደራል እና/ወይም የክልል ም/ቤቶች በሚያቀርባቸው እጩዎች ብዛት የሚደለደል- 40 በመቶ
- ፓርቲው በሚያቀርበው የሴት እጩ ተወዳዳሪዎች ብዛት የሚደለደል 20 በመቶ
- ፓርቲው በሚያቀርበው የአካል ጉዳተኛ እጩዎች ብዛት የሚደለደል 10 በመቶ መሆኑ ላይ ውይይት ተደርጓል ሲል ቦርዱ ገልጿል፡፡