እንግሊዝ በኳታር የፊፋ ዓለም ዋንጫ ግጥሚያ ኢራንን በበርካታ ግቦች ረታች

እንግሊዝ ኢራንን የረታችው 6 ለ 2 በሆነ ውጤት ነው።

England v IR Iran.jpg

Bukayo Saka of England scores to make it 2-0 during the FIFA World Cup Qatar 2022 Group B match between England and IR Iran at Khalifa International Stadium on November 21, 2022 in Doha, Qatar. Credit: Ian MacNicol/Getty Images

የእንግሊዝና ኢራን ግጥሚያ በርካታ ግቦች የተቆጠሩበት ቢሆንም ለአሸናፊነት ለመብቃት ብርቱ ፍልሚያ መታየት የጀመረው የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ዘግየት ብሎ ነው።

ግብ ማስቆጠር ሲጀመር ግና በመጀመሪያው አጋማሽ ጨዋታ በ11 ደቂቃዎች ውስጥ ሶስት ግቦች ተቆጥረዋል።

በሁለተኛው አጋማሽም ፍልሚያው ጠንክሮ፤ ጥቃቱ በርትቶ ታይቷል።

የግጥሚያው ጠቅላላ ውጤትም እንግሊዝ 6 ኢራን 2 ግቦችን በማስቆጠር ተጠናቅቋል።

ለእንግሊዝ ቡካዮ ሳካ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል።

Bukayo Saka of England in action during the FIFA World Cup Qatar 2022 .jpg
Bukayo Saka of England in action during the FIFA World Cup Qatar 2022 Group B match between England and IR Iran at Khalifa International Stadium on November 21, 2022 in Doha, Qatar. Credit: Ian MacNicol/Getty Images

ምንም እንኳ ኢራን 6 ለ 2 በእንግሊዝ ብትረታም፤ የኢራኑ አሰልጣኝ ካርሎስ ከሮሽ የእንግሊዝ ቡድን በርትቶ በመጫወት ለድል መብቃቱን ጠቅሰው፤ የራሳቸውንም ተጫዋቾች በአዋኪ ሁኔታ ብርቱ ፍልሚያ ማድረግ እንደቻሉና በሚቀጥሉት ሁለት ግጥሚያዎች የተሻለ ውጤቶችን ማስመዝገብ እንደሚችሉ ተናግረዋል።


1 min read

Published

By Kassahun Seboqa Negewo, NACA

Source: SBS



Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now