ዛሬ ጠዋቱን በተከናወነው የ6ተኛው የስራ ዘመን 4ተኛ ልዩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ የ2014 የኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት 561.7 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀድቋል።
በጀቱ 162.17 ቢሊየን ብሩ ለመደበኛ ወጭ፤ 183.55 ቢሊየኑ ለካፒታል ወጭ ፤ 203.95 ቢሊየን ለክልሎች ድጋፍ እንዲሁም 12.00 ቢሊየን ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ይውላል፡፡

Source: Ethiopian Parliament
የ2014 የፌደራል መንግስት ጠቅላላ ገቢ ከታክስ 334.01 ፤ ታክስ ካልሆኑ 35.10 እንዲሁም መሰረታዊ አገልግሎት ከለላ እርዳታ 38.75 እና ፕሮጀክት እርዳታ 28.06 ቢሊዮን እንደሚሰበሰብ ተገልጿል፡፡

Source: Ethiopian Parliament
በ2014 ዓ.ም ከተያዘዉ በጀት መካከል መንገድ 67.45 ቢሊየን፤ ትምህርት 66.06 ቢሊየን ፤ ዕዳ ክፍያ 45.12 ፤ መከላከያ 22.00 ቢሊየን ብር እና ጤና 20.43 ቢሊየን ብር የተመደበላቸው ቀዳሚ ሴክተሮች ሆነዋል።
[ ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ ]