በጦርነቱ ሳቢያ የተፈናቀሉት ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የአለም አቀፍ ለጋሾች ፈቃዳቸውን ማሳታቸው ተገለጸ
በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም ከዓለም አቀፍ ለጋሾች ጋር ውይይት መደረጉን የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል አስታወቁ።
ከዚህ በፊት ባጋጠሙን የተለያዩ ተፈሯዊም ይሁን ሰው ሰራሽ አደጋዎች ላይ አስቸኳይ እርዳታ በማቅረብ ቀና ትብብራቸውን ያሳዩ ተቋማት አሁንም ባጋጠሙ ችግሮች ትብብራቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ሚንስትሯ በማህበራዊ ገፃቸው አስታውቀዋል።