ነገ ለሚካሄደው ምርጫ ደህንነት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ

*** በመላው የፌዴራል እና የክልል ማዘዣ ጣቢያዎች ባሉ የመረጃ መጋራት መሳሪያዎች፣ የሳተላይት ቁጥጥር ስርዓቶች እና የድሮን ቴክኖሎጂ ለዚሁ ዝግጅት መሰማራቱም ተነግሯል

SBS Amharic

Source: SBS Amharic

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዶር ዐቢይ አሕመድ የነገውን የምርጫ ቀን አስመልክቶ ዛሬ ከብሔራዊ ምርጫ ደህንነት ስትራቴጂ ማዘዣ ጋር እንደተወያዩ በማህበራዊ ትስስር ገፆቹ ገልጿል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በማዕከላዊ ዕዝ የሁኔታ ክትትል ክፍል ውስጥ ይፋ የተደረገው የብሔራዊ መረጃና ደህንንነት አገልግሎት የምርጫ ደህንነት መድረክ  በምርጫ ደህንነት ዘርፍ የተከናወነውን ዝግጁነት እንደገመገመ ነው የተገለፀው።

" የደህንነቱ ዝግጁነት በሁሉም የሀገሪቱ ማእዘናት ላይ አካላዊ ኃይል ማሰማራትን እንዲሁም የሳይበር ደህንነት ማሻሻያዎችን የተመለከቱ ስጋቶችን ማክሸፍን ያጠቃልላል።" ብሏል ጽህፈት ቤቱ ያወጣው መግለጫ
Election security
Election security meeting Source: PMOE
በመግለጫው እንደተጠቀሰው "በመላው የፌዴራል እና የክልል ማዘዣ ጣቢያዎች ባሉ የመረጃ መጋራት መሳሪያዎች፣ የሳተላይት ቁጥጥር ስርዓቶች እና የድሮን ቴክኖሎጂ ለዚሁ ዝግጅት ተሰማርተዋል" ተብሏል።

በመግለጫው ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ይህንን አዲስ አካሄድና ከብሔራዊ ቁልፍ ተግባራት ቀድሞ ብሔራዊ ደህንነትን በማረጋገጥ ረገድ የተፈጠረውን አቅም " እንደተመለከቱ ተገልጿል።

በምርጫው ወቅት ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ የፀጥታ ስጋቶችና አጠቃላይ የቦርዱን ዕቅድ አፈፃፀም በተመለከተ ከሰሞኑ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከ ኤስ ቢ ኤስ አማርኛ ዘጋቢ ለቀረበ ጥያቄ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስ በእስካሁን የቦርዱ ምልከታና ከፀጥታ ተቋማት ካገኙት መረጃ እንደተገነዘቡት የምርጫ ሂደቱን ሊያውክ የሚችል ጉልህ የፀጥታ ችግር ሊያጋጥም እንደማይችል እምነታቸው መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል።

[ ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ ]


Share

Published

By Demeke Kebede

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service