ኢሰመኮ በምርጫው ወቅት የሕግ አስከባሪ አካላት ሰብዓዊ መብቶችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ አሳሰበ

*** “የሕግ አስከባሪ አካላት ሰብአዊ መብቶችን አክብረው ተግባራቸውን ለማከናወን የገቡትን ቃልኪዳን በምርጫው ሂደት በተግባር በመተርጎም የምርጫ ሂደቱ ሰብአዊ መብቶች የተረጋገጡበት እንዲሆን በቁርጠኝነት መስራት ይገባቸዋል” - የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

Dr Daniel Bekele,

Dr Daniel Bekele, Chief Commissioner of Ethiopian Human Rights Cpmmission. Source: D.Bekele

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በምርጫ ሂደት የሰብዓዊ መብት ጥበቃን በሚመለከት ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ምርጫ በሚካሄድባቸው ሁሉም ክልሎች ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ ምክክሮችን አከናውኗል።

ምክክሮቹ የተከናወኑት ከአዳማ፣ ከጅማ፣ ከባሕር ዳር፣ ከሃዋሳ፣ ከጋምቤላ፣ ከአሶሳ እና ከሰመራ ከተሞች ፖሊስ እና የፍትህ አካላት ከተውጣጡ መካከለኛ አመራሮች ጋር ነው።

ኮሚሽኑ የምክክር መድረኮቹን ያከናወነው የሕግ አስከባሪ አካላት ካለባቸው ሰብአዊ መብቶችን የማክበር፣ የማስከበር እና የማሟላት ኃላፊነት አኳያ፣ በቅድመ ምርጫው፣ በምርጫው ዕለትና በድኅረ-ምርጫው ወቅት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ የሕግ አስከባሪ አካላትን ግዴታና ኃላፊነቶች ለማስታወስ ነው።

በተለይም ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ፣ የመዘዋወር፣ የመሰብሰብ እና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቶችን ጨምሮ ሌሎች በምርጫ ወቅት ትኩረት የሚሹ ሰብአዊ መብቶችን በማረጋገጥ ረገድ የሕግ አስከባሪ አካላት ሚና በዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸዋል። የሕግ አስከባሪ ተቋማት ባልደረቦችም ተግባራቸውን ሰብአዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ ለማከናወን ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።

ኢሰመኮ በምርጫው ወቅት የሕግ አስከባሪ አካላት በገለልተኝነት ተግባራቸውን በመወጣት የዜጎች መብቶችን እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ እንዲሁም ጥሰቶች ሲኖሩ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ በአጽንዖት አሳስቧል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “የሕግ አስከባሪ አካላት ሰብአዊ መብቶችን አክብረው ተግባራቸውን ለማከናወን የገቡትን ቃልኪዳን በምርጫው ሂደት በተግባር በመተርጎም የምርጫ ሂደቱ ሰብአዊ መብቶች የተረጋገጡበት እንዲሆን በቁርጠኝነት መስራት ይገባቸዋል” ብለዋል። 


Share

Published

By Stringer Report

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
ኢሰመኮ በምርጫው ወቅት የሕግ አስከባሪ አካላት ሰብዓዊ መብቶችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ አሳሰበ | SBS Amharic