የኢትዮጵያ መንግስት ህይል የመቀሌን ከተማ መክበቡን ካስታወቀ በኋላ ውጥረቱ እየተባባሰ ሂዷል ፡፡ የትግራይ ህዝቦች ነጻነት ግንባር መሪዎች እጃቸውን እንዲሰጡ መንግስት ያወጣው የ 72 ሰአታት ገደብ ሊጠናቀቅ የቀረው ጥቂት ነው፡፡
ጥቅምት 25 በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተጀመረውን ወታደራዊ ዘመቻ ለማጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሀይል በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ መንገስት የትግራይ ህዝቦች ነጻነት ግንባር ሁለት ወታደራዊ ካምፖችን በማጥቃት እና ክህደት በመፈጸም መንግስትን እንዳይረጋጋ አድርጓል ሲል ግንባሩን ተጠያቂ ያደርጋል ፡፡
የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን የተጣለውን ገደብ አስመልከተው ለትግራይ ክልልን ነዋሪዎች ማስጠንቀቂያን ሰጥተዋል ፡፡
“ የመጨረሻው መጀመሪያ ላይ ተቃርበናል ፤ የመከላከይ ህይላችን የመቀሌ ከተማን ሙሉ ለሙሉ ከቧል፤ መሳሪያ ተከማችቶባቸውል የተባሉት ቦታዎች ዋናው የጥቃት ኢላማዎች ናቸው፡፡ ” ብለዋል
አቶ ሬድዋን አያይዘውም “ በዮኔስኮ ቅርስ ማህደር ውስጥ የተመዘገበቸው የአክሱም ከተማ በሸሹት የትግራይ ሚሊሻ እና ልዩ ሀይሎች ክፉኛ ጉዳት ደርሶባታል ፤ የአክሱም አየር ማረፊያን በማጥቃትም የአውሮፕላን ማኮብኮቢያ ስፍራውን በቡልዶዘር አርሰውታል ፤መገልገያ ቁሳቁሶችንም አውድመዋል፡፡ ” ሲሉ ተናግረዎ ፡፡
የትግራይ ህዝቦች ነጻነት ግንባር መሪዎች ለተፈጸመው ውድመት ሃላፊነትን እንደማይወስዱ እና የመቀሌ ከተማ ተከባለች መባሉንም አስተባብለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሽብር ጥቃን በዋና ከተማዋ ሊፈጽሙ ሲሉ ተገኝተዋል ብሎ የጠረጠራቸውን 800 ሰዎች ፖሊስ በቁጥጥር ስል ማዋሉን አስታውቋል ፡፡
እንደ ተባበሩት መግስታት ድርጅት ግምት ከሆነ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ጀምሮ 17,000 የሚሆኑ ህጻናትን ጨምሮ 40,000 የሚሆኑ ሰዎች ሲፈናቀሉ በሺህ የሚቆጠሩት ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጀነራል ሴክረታሪ ቃል አቀባይ ስቴፈን ጁሪክ በትግራይ ክልል የሚገኙ ሰላማዊ ሰዎች ደህንነት እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል ፡፡
“ ሁለት መቶ የሚሆኑ የእርዳታ ሰራተኞችን ጨምሮ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በመቀሌ ከተማ ቀርተዋል ፡፡በወጣው መረጃ መሰረትም ጦርነቱ በቅርቡ ሊጀመር ይችላል ፡፡ እኛ እና በሰብአዊ ምግባር ላይ ተሰማርተው ያሉት አጋሮቻን የምንጠይቀው ሁለቱም ቡድኖች በአለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግ እና ግዴታዎች እንዲመሩ ፤ ሰላማዊ ዜጎችን እንዲከላከሉ የሚጠቀሚባቸውን የመሰረተ ልማት አውታሮች የጤና እና የውሃ ተቋማትን ከአደጋ እንዲከላከሉ ነው ፡፡” ብለዋል
ከትግራይ ወደሱዳን ከተሰደዱት እና በሺዎች ከሚቆጠሩት ተፈናቃዮች መካከል አንዱ የሆኑት አብደንዶን ተክለማርያም ሲናገሩ “ እጅግ አስቸጋሪ ነበር ፤ ተርበን ነበር የምንጠጣው ውሃም አልነበረም ፤ ምግብም መጓጓዣም አልነበረም ” ብሏል
ሌላኛው ስደተኛ ሀፍቶም በርሄ ጦርነቱ ሲጀመር ቤተሰቡን በመያዝ እንደተሰደደ ተናግሯል ፡፡“ ያለኝን ንብረት በሙሉ ትቼ ነው የተሰደድኩት ፤ ከወላጆቼ እና ቤተሰቤ ጋር ብቻ ነው የተሰደድኩት ምንም ነገር ይዘን አልመጣንም ፤ተለዋጭ አልባሳትም የሉንም ፤አሁንም ድረስ ክዚያ መውጣት ያልቻሉ በርካታ ሰዎች አሉ ብዙ ናቸው ባጣም ያሳዝናል ፡፡ ”