ዝነኛው የዌልሽ ብሔራዊ መዝሙር "የአባቶቻችን መሬት" ከ1958 ወዲህ በዓለም ዋንጫ መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ ዶሃ ላይ ሲዘመር፤ ባለፈው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ማለፍ ተስኖት የቀረው የዩናይትድ ስቴትስ ቡድንም በስምንተኛ ዓመቱ ለዓለም ዋንጫ ውድድር ኳታር ለመገኘት በቅቷል።
በሁለቱ ቡድናት ግጥሚያ ወቅት የመጀመሪያውን ግብ በ36ኛዋ ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው የላይቤሪያው ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋችና የወቅቱ የላይቤሪያ ፕሬዚደንት ጆርጅ ዌየር ልጅ ቲሞቲ ዌየር ነው።
ይሁንና ለ70 ዓመታት ርቆ የቆየው የዌልስ ቡድን በዜሮ መለየትን አልመረጠም።
ብርቱ ፍልሚያ እያካሔደ ሳለ የዩናትድ ስቴትሱ ተከላካይ ዎልከር ዚመርማን በዌልሹ የቡድን አምበል ጋሬት ባሌ ላይ በ80ኛዋ ደቂቃ በፈፀመው ጥፋት ለቀይ ካርድ ተዳርጓል። ጥፋቱም የፍጹም ቅጣት ምትንም ለዌልስ ቡድን አስችሯል።
ባሌ ጊዜ ሳያጠፋ የፍጹም ቅጣት ምቷን ለግብነት አብቅቶ ዌልስና ዩናይትድ ስቴትስ 1 ለ 1 እንዲለያዩ አስችሏል።

Gareth Bale of Galler celebrates after scoring a goal during the FIFA World Cup Qatar 2022 Group B match between USA and Wales at Ahmed bin Ali Stadium in Al-Rayyan, Qatar on November 21, 2022. Credit: Mustafa Yalcin/Anadolu Agency via Getty Images
ከቡድን "ሀ" በአንደኛ ደረጃነት ለቀጣዩ ማጣሪያ ያልፋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የኔዘርላንድስ ቡድን በመጀመሪያ ግጥሚያው ተቀናቃኙን ሴኔጋልን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ድል ነስቷል።
ግቦቹ የተቆጠሩት የጨዋታው መጠናቀቂያ ሰዓት በተቃረበበት በ83ኛው ደቂቃ በኮዲ ጋክፖ እና ለፍፃሜ ጥቂት ደቂቃዎች ጉዳይ ላይ በፍሬንኪ ዴ ያንግ አማካይነት ነው።

Cody Gakpo of Holland during the FIFA World Cup Qatar 2022 group A match between Senegal and Netherlands at Al Thumama Stadium on November 21, 2022 in Doha, Qatar. Credit: ANP MAURICE VAN STONE via Getty Images