የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28 እንዲሆን በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ላይ አሳውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ እና የድሬደዋ ከተማ መስተዳድር የድምጽ መስጫ ቀን ሰኔ 5 መሆኑን ገልጿል።
ቦርዱ ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳውን ይፋ አድርጓል።
ይህ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ የትግራይ ክልልን አያካትትም ተብሏል።
የምርጫ ቢሮዎች መከፈት የክልል መስተዳድር አባላት ከፍተኛ ትብብር ስለሚያስፈልገው፤ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ይህንን ድጋፍ ለማድረግ ጊዜ ስለሚያስፈልገው እንዲሁም በክልሉ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለምርጫ በሚስማማ መልኩ መመቻቸቱ ሲረጋገጥ በክልሉ የሚደረገው ምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ቦርዱ የሚያሳውቅ ይሆናል።

Ethiopia's general elections timetable Source: NEBE
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም የድምጽ መስጫ ቀን እንዲሆን ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ አቅርበው ዛሬ ውይይት ተደርጎበታል።
የቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫን የጊዜ ሰሌዳ አስመልክቶ ቦርዱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በአዲስ አበባ ራዲሰን ብሉ ሆቴል ተወያይቷል፡፡
በዚህ ስብሰባ በ2013 የሚደረገው ምርጫ አጠቃላይ የትግበራ መርሃ ግብር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡