"ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የነፃነት አርማችን ነው" - ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ

*** የሕዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ 160 ቢሊዮን ብር ይፈጃል

GERD Budget

Eng. Kifle Horo Source: Courtesy of PMOE

ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ በኮንትራት መልኩ ተበጅቶ የነበረው ጠቅላላ በጀት 78.3 ቢሊዮን ብር ቢሆንም የግንባታው ሂደት ግና እስካሁን 120 ቢሊዮን ብር መፍጀቱን የሕዳሴ ግድብ ፕሮጄክት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ አስታውቀዋል።

አያይዘውም፤ የግድቡን ግንባታ ለማጠናቀቅ 160 ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ አመላክተዋል።

የፕሮጄክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ይህን የገለጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ከሕዳሴው ግድብ የቦርድ አመራሮችና አግባብ ካላቸው የፌዴራል መንግሥቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

በውይይቱ ወቅት የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ 78 በመቶ መድረሱን፤ የአሌሌክትሮ ሜካኒካል ሥራው 46.5 በመቶ እንዲሁም የሲቪል ክንዋኔው 88.8 በመቶ መድረሱ ተገልጧል።

 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የግድብ ግንባታውን ዳር የመድረስ እሳቤ አስመልክተው የተያዘውን በውል ውጥን ግብር ላይ ማዋል ከተቻለ በ2015 ግድቡ ለምረቃ እንደሚበቃና አስፈላጊው ሙሉ ድጋፍና ክትትል ተደርጎለት ነሐሴ 2013 ላይ 18.4 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ መያዝ እንደሚችል ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ታላቁ የህዳሴ ግድብ የነፃነት አርማችን ነው" ሲሉም የግድቡን አገራዊ ተምሳሌነት ሉዓላዊ ግዘፍ አላብሰው ገልጠዋል።    


Share

Published

Updated

By Stringer Report

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
"ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የነፃነት አርማችን ነው" - ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ | SBS Amharic