የኒው ሳውዝ ዊልስ ፕሪምየር ግላዲስ በርጂክልያን ከስልጣናቸው ለቀቁ ፡፡
የኒው ሳውዝ ዊልስ ፕሪምየር ግላዲስ በርጂክልያን ከስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ያሳወቁት ፤ የጸረ ሙስና ኮምሽን ምርመራ እንደሚያደርግባቸው ካስታወቀ በኋላ ነው ፡፡
ገለልተኛ የሆነው ጸረ ሙስና ኮምሽን በዛሬው እለት እንዳሳወቀው ፤ ሚስ በርጂክልያን ከስልጣላቸው ከተባረሩት የፓርላማ አባል ዳሪይል ማጓየር ጋር በመሆን የመንግስትን አመኔታ የሚጥስ ተግባር መፈጸም አለመፈጸማቸውን ለማረጋገጥ ይፋዊ የሆነን ስሚ እንደሚያደርግ ነው ፡፡
ሚስ በርጂክልያን የዋጋ ዋጋ የቀድሞ የሊብራል ተወካይ ከነበሩ ሰው ጋር የግል ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን ፤ ግለሰቡም የመግስት ቢሮን አና የፓርላማን ሀብትን የግል ሀብትን ለማካበት መጠቀማቸው ተርጋግጦባቸዋል፡፡
በርጂክልያን ከፓርላማ አባልነታቸውም ራሳቸውን እንደሚያገልሉ ተናግረዋል፡፡፡