ከ300 ሺህ በላይ ለሆኑ የአፋርና አማራ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ እርዳታ ቀረበ

*** 318 የሰብዓዊ እርዳታዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቀሌ ደርሰዋል

Food distribution.

Food distribution. Source: Getty

የኢትዮጵያ መንግሥትና የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሕወሓት ጥቃቶች የተነሳ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ለተፈናቀሉ ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች የሰብዓዊ ዕርዳታ እያቀረቡ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ትናንት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ፕሬስ ሴክሬተሪያት የውጭ ቋንቋዎች እና ዲጂታል ሚዲያ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም እንዳሉት እስከ ነሐሴ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ 318 የሰብዓዊ እርዳታዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቀሌ ደርሰዋል፤ በሕወሓት ጥቃቶች የተነሳ ከአማራና ከአፋር ክልሎች ለተፈናቀሉ ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች የኢትዮጵያ መንግሥት እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ሰብዓዊ ዕርዳታ እያቀረቡ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
Humanitarian Aid.
Humanitarian Aid. Source: Getty


በአማራ እና በአፋር ክልሎች ሕዝብ እያሸበረ፤ የሕክምና ተቋማትን ጨምሮ የግለሰቦችን ሀብትና ንብረት እየዘረፈ፤ የመሰረተ ልማት አውታሮችን እያወደመ፣ በወረራ በገባባቸው ንጹሃንን እያሰቃየና እየገደለ ነው ሲሉ የተናገሩት ቢልለኔ ሕወሓት ትናንትና በደብረ ታቦር ከተማ በተኮሳቸው ከባድ መሳሪያዎች ንጹሃንን ገድሏል ብለዋል፡፡

"ሕወሓት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ በአጠቃላይ የሰላም እና ጸጥታ ችግር ነው፤ ስለሆነም ሁሉም ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ወዳጆች የሽብር ቡድኑ በአፍሪካ ቀንድ ካሉ ዓለም አቀፍ የሽብር ቡድኖች ጋር እያደረገ ያለውን ትብብር በጥንቃቄ ሊመለከቱትና ሊያወግዙት ይገባል” ሲሉም አክለዋል፡
Homeland Report
Press Secretary for the Office of the PMO Ethiopia Billene Seyoum Woldeyes speaks to press regarding the current issues in Tigray, in Addis Ababa, on August 13. Source: Getty
ቢልለኔ በመግለጫቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቱርክ ጉብኝት በትብብር ስምምነቶች የተቋጨ፣ የአቀባበል ድምቀት የነበረውና የተሳካ እንደነበርም አውስተዋል፡፡

( ደመቀ ከበደ - አዲስ አበባ)


Share

Published

By Demeke Kebede

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
ከ300 ሺህ በላይ ለሆኑ የአፋርና አማራ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ እርዳታ ቀረበ | SBS Amharic