ኢሰመኮ በምርጫው ዕለት የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ለማድረግ ባለሙያዎች ማሰማራቱን አስታወቀ

*** ኮሚሽኑ ማንኛውም ሰው በነገው ዕለት በሚካሔደው ብሔራዊ ምርጫ ወቅት ለክትትል ቡድኑ አባላት ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ መረጃ እና ጥቆማ ማቅረብ የሚችል ሲሆን፤ ከዚህም በተጨማሪ በኮሚሽኑ የነፃ የስልክ መስመር 7307 ላይ በመደወል መረጃ መስጠት እንደሚችል ገልጧል፡፡

SBS Amharic

Source: SBS Amharic

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተሻሻለው የማቋቋሚያ አዋጁ አንቀፅ 6 መሰረት በምርጫ ወቅት የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅን ክትትል የማድረግ ስልጣን እና ሀላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ በዚህም መሰረት ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. በሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ የሰብአዊ መብቶችን ሁኔታ ለመከታተል የምርጫ ክትትል ቡድኖች በማቋቋም ምርጫ በሚካሄድባቸው በሁሉም ክልሎች ባለሙያዎችን አሰማርቷል፡፡

የኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ምርጫ ክትትል ቡድኖች በሚሰማሩባቸው ስፍራዎች በምርጫው እለት እና ከምርጫው በኋላ ባሉት ቀናት በምርጫ ጣቢያዎችም በመገኘት ምልከታ ያደርጋሉ፤ መራጮችን፣ የምርጫ አስተባባሪዎችን፣ የፀጥታ አካላትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ እጩዎችን፣ ታዛቢዎችን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማነጋገር መረጃዎችን ያሰባስባሉ፡፡ በፖሊስ ጣቢያዎች እና በሕክምና ተቋማት በመገኘትም አስፈላጊውን ክትትል ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

ማንኛውም ሰው እና ተቋማት በሙሉ የኮሚሽኑን መለያ ካርድ (ባጅ) በመያዝ ለሚሰማሩት የኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ምርጫ ክትትል ቡድን አባላት አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ ይገባል፤ እንዲሁም ማንኛውም ሰው ለክትትል ቡድኑ አባላት ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ መረጃ እና ጥቆማ ማቅረብ የሚችል ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በኮሚሽኑ የነፃ የስልክ መስመር 7307 ላይ በመደወል መረጃ መስጠት እንደሚችል ኮሚሽኑ አሳውቋል፡፡  

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በምርጫው ወቅት ሰብአዊ መብቶች መከበራቸውን ማረጋገጥ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነት መሆኑን አስታውሰው ‹‹በኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ በግልፅ በተቀመጠው መሰረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለኮሚሽኑ ስራ መሳካት ትብብር የማድረግ ግዴታቸውን እንዲወጡ እና በክትትል ስራ ለሚሰማሩት የኮሚሽኑ ባለሙያዎች አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ›› ጥሪ ማቅረባቸውን ኮሚሽኑ ለ SBS አማርኛ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ቀደም ሲል የምርጫ ቦርድ የመተዳደሪያ ደንቡን አንቀጽ 123 በመጥቀስ ኢሰመኮ አቅርቦት የነበረውን የምርጫ ተመልካችነት ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል። ስለ ጉዳዩ ዕልባት ማግኘት ወይም አለማግኘትን አስመልክቶ ከሁለቱም ድርጅቶች በኩል እስካሁን በይፋ የተሰጠ ማብራሪያ የለም።  

ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ


Share

Published

By Demeke Kebede

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service