"ጊዜው አሜሪካን የመፈወሻ ነው" - ጆ ባይደን

*** "የመጀመሪያዋ [የዩናይትድ ስቴትስ] ሴት ምክትል ፕሬዚደንት ብሆንም የመጨረሻዋ ግን አልሆንም" - ካማላ ሃሪስ

Joe and Kamala

Source: AAP

ጆ ባይደን ለዩናይትድ ስቴትስ 46ኛው ተመራጭ ፕሬዚደንት ከሆኑ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረጉት ንግግር እሳቸውን ደግፈውም ይሁን ተፃርረው ለመረጡ አሜሪካውያን ሁሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ታትረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

"ጊዜው የከረሩ አባባሎችን መክሊያ፣ ግለትን ማብረጃ፣ አንዳችን ካንዳችን ጋር መተያያና አንዳችን አንዳችንን ማድመጫና ወደፊት መራመጃ ነው፤ ተቀናቃኛችንን በጠላትነት መመሰሉን ማቆም አለብን" ብለዋል። 

አቶ ባይደን በንግግራቸው ወቅት ዶናልድ ትራምፕን ስም አልጠቀሱም። ቅድሚያ ከሚሰጧቸው ዋነኛ አጀንዳዎቻቸው ውስጥ ኮቨድ - 19ን በቁጥጥር ስር ማዋል፣ የምጣኔ ሃብት እንዲያንሰራራ ማድረግ፣ ለዘር መድልዖ ፍትሕ ማስገኘትና የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል እንደሆነ ጠቁመዋል። 

አብረዋቸው ለምክትል ፕሬዚደንትነት ለድል የበቁትን ካማላ ሃሪሰን "የመጀመሪያ ጥቁር ሴት፣ ከደቡብ እስያ ዝርያ የመጀመሪያዋ ሴት፣ በአገራችን ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ተመራጭ" በማለት ስኬታቸው ታሪካዊ መሆኑን ተናግረዋል።
Vice President-elect Kamala Harris.
Vice President-elect Kamala Harris. Source: AFP
ካማላ ሃሪስም በበኩላቸው "ለዚህ ቢሮ የመጀመሪያዋ ሴት ብሆንም፤ የመጨረሻዋ ግን አልሆንም" ብለዋል።

ጆ ባይደን 46ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት በመሆን ከተመራጭ ምክትል ፕሬዚደንት ካማላ ሃሪስ ጋር ጃንዋሪ 20 ቃለ መሃላ በመፈጸም ፕሬዚደንታዊ ስልጣን ተረክበው ኃላፊነታቸውን መወጣት ይጀምራሉ።

 


Share

Published

By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
"ጊዜው አሜሪካን የመፈወሻ ነው" - ጆ ባይደን | SBS Amharic