በዘንድሮው 2020 ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የጆ ባይደን በ77 ዓመት ዕድሜያቸው 46ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ሆኖ መመረጥ ብቻ ሳይሆን በአባታቸው የጃማይካና በእናታቸው የሕንድ ዝርያ ያላቸው ካማላ ሃሪስም የመጀመሪያዋ ሴት ጥቁር ፕሬዚደንት ሆኖ መመረጥም በዩናይትድ ስቴትስ የታሪክ ባሕር መዝገብ ውስጥ ልዩ ሥፍራ ይዟል።
ወይዘሮ ሃሪስ የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል ሆነው ከመመረጣቸው በፊት የካሊፎርኒያ የመጀመሪያዋ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሆነው አገልግለዋል።
ካማላ ምንም እንኳ የእሳቸው ስኬት አያሌዎችን በሕይወታቸው ውስጥ ከፍ ላለ ውጤት እንዲያልሙ ቢያነቃቃም ለሳቸው የሕይወት ስኬት አርአያ የሆኑት እናታቸው እንደሆኑ ሲናገሩ "በሕይወቴ ውስጥ ታላቋ የመንፈስ መነቃቃት ምንጬ እናቴ ሽያማላ ጎፓላን ሃሪስ ናት"

Kamala Harris and her husband Douglas Emhoff at an election eve rally on 2 November. Source: Getty Images
"እኔንና እህቴ ማያን ታትሮ የመሥራትንና ህፀፆች ሲፈጸሙም የማረምን አስፈላጊነት አስተምራናለች" ብለዋል።
የፔንሲቫኒያን ውጤት ተከትሎ የሳቸውና የጆ ባይደን አሸናፊት እንደተገለጠ ለባይደን ደውለው የጋራ አሸናፊነታቸውን ብሥራትና የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የሕግ ባለ ሙያ የሆኑት ባለቤታቸው ዳግላስ ኢምሆፍም የመጀመሪያው እስራኤላዊ - አሜሪካዊ የምክትል ፕሬዚደንት ባል በመሆን ራሳቸውን በአሜሪካ ታሪክ ልዩ ስፍራ አስመዝግበዋል።

Kamala Harris Source: SBS
ውጤቱን ተከትሎም በባለቤታቸው ስኬት ክብር የሚሰማቸው መሆኑን ገልጠዋል።
የቀድሞዋ ቀዳሚዊት እመቤት ሚሼል ኦባምም ለጆ ባይደንና ለካማላ ሃሪስ የደስታ መልዕክታቸውን ልከዋል።
የካማላ ሃሪስ ምርጫ የሆሊውድ ተዋናይቱን ሚንዲ ካሊንግን የደስታ ዕንባ ያስነባ ሲሆን ኮሜዲያን ጁሊያ ሉዊስ - ድሪፈዝንም ከእንግዲህ “Madam Vice President” የሚለው ከልብ ወለድ የሆሊውድ ፊልምነት አልፎ ዕውን ሆኗል አስብሏል።


Douglas Emhoff Source: DE

Source: Michelle Obama

Source: Mindy Kaling

Source: Julia Louise-Dreyfus