ሌበር የኩዊንስላንድ ስቴት ምርጫን አሸነፈ

*** የጄምስ ቦንድ አክተር ሾን ኮነሪ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

QLD State election

Queensland Premier Annastacia Palaszczuk is seen giving her victory speech to supporters at The Blue Fin Fishing Club in Brisbane Source: AAP

አናስታዥያ ፓለሼ ለሌበር ፓርቲ የኩዊንስላንድ ስቴት ምርጫን በማሸነፍ ድል ሲያጎናጽፉ ለራሳቸውም ሶስት ምርጫ በማሸነፍ በአውስትራሊያ ፖለቲካ ታሪክም የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን የታሪክ ባሕር መዝገብ ውስጥ ስማቸውን አኑረዋል።

በ2021 አጋማሽ ከሁለተኛው ጦርነት በኋላ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ የአውስትራሊያ ሴት መሪ የሚሆኑ ሲሆን በ2024 አጋማሽ የሌበር ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ፕሪሚየር ይሆናሉ።  

ፕሪሚየር ፓለሼ ትናንት ምሽት የምርጫ ድል እንዲጎናጸፉ ድምጻቸውን ለሰጧቸውና ላልሰጧቸው የኩዊንስላድ መራጮች 2020 በኮረናቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ አዋኪ ዓመት እንደነበረና በጋራ ተባብሮ ስለመቆም ጠቀሜታ አንስተው ሲናገሩ፤

"በሉላዊ ወረርሽኝ መሃል ሆነን ወደ ሌላ ስቴት ሲልም በዓለም ዙሪያ ተጉዛችሁ ቤተሰቦቻችሁንና ጓደኞቻችሁን ማየት ባለመቻላችሁ በእጅጉ አዋኪ ነበር" 

"ይሁንና እዚህ ኩዊንስላንድ ውስጥ ጠንክረን በአንድነት ቆመናል፤ በጋራም ወረርሽኙን ተቆጣጥረናል። በአንድነት ሆነን መሥራቱን ከቀጠልን ጠንክረን እንዘልቃለን" ብለዋል።

አክለውም፤ የኩዊንስላንድ ሕዝብን ለማገልገል ከቡድናቸው ጋር ሆነው እጅጌያቸውን በመሰብሰብ በተቻለ ፍጥነት ወደ ሥራ ለመግባት ቁርጠኝነታቸውን በመግለጥ የሌበር መንግሥት አብላጫ የምክር ቤት ወንበሮችን አሸንፎ ራሱን ችሎ መንግሥት እንደሚያቆም ያላቸውን እምነት ገልጠዋል። 

ሌበር ፓርቲ ወደ ምርጫ ከመግባቱ በፊት ከ93 የኩዊንስላንድ ምክር ቤት ወንበሮች ውስጥ 48 የምክር ቤት ወንበሮች ነበሩት።   

በABC የምርጫ ኮምፒዩተር ስሌት መሠረት ሌበር 52 ወንበሮችን ሊብራል-ናሽናል 34 ወንበሮችን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ተተንብዮዋል።
QLD State election
Source: ABC Australia
የሊብራል - ናሽናል ፓርቲ መሪ ዴብ ፍሬክሊንግተን በምርጫ ድል መነሳታቸውን አስመልክተው ሲናገሩ፤

"ኩዊንስላንዳውያን ውሳኔያቸው አሳልፈዋል፤ ለዲሞክራሲያችን ዘለቄታ ድምጻቸውን የሰጡትን ሁሉ አመሰግናለሁ" ብለዋል።
QLD State election
Queensland Opposition Leader Deb Frecklington speaks to supporters in Brisbane. Source: SBS
አክለውም የኩዊንስላንድን ሕዝብ በሊብራል - ናሽናል ተቃዋሚ ቡድን መሪነታቸው ማገልገላቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

ሌበር ፓርቲ ወደ ምርጫ ከመግባቱ በፊት ከ93 የኩዊንስላንድ ምክር ቤት ወንበሮች ውስጥ 32 የምክር ቤት ወንበሮች ነበሩት።   

ጄምስ ቦንድ

 

የልብ ወለድ ዓለሙን ሰላይ ጄምስ ቦንድ ገጸ ባህሪ በመተወን ዝናን የተጎናጸፉት ተዋናይ ሾን ኮነሪ በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የተዋናይ ሾን ልጅ ጄሰን አባታቸው ለተወሰነ ጊዜ ጤናማ እንዳልነበሩና ትናንት ለሊቱን ባሃማስ ዕንቅልፍ ሳሉ ማለፋቸውን ለBBC ገልጠዋል።
actor Sean Connery
Sean Connery leads a procession up New York's Sixth Avenue as part of a bagpipe band of about 10,000 people on 6 April 2002. Source: AAP
ስኮትላንዳዊው ተዋናይ ለበርካታ አሠርት ዓመታት በዘለቁበት የትወና ሙያቸው ስኬት አንድ የኦስካር፣ ሶስት ጎልደን ግሎብስና ሁለት የባፍታ ሽልማቶችን ተቀብዋል።

 


Share

Published

Updated

By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service