ቦርዱ ለአገራዊ ምርጫ ኦፕሬሽን እያደረገ ያለውን ዝግጅት እና በተለያዩ መጋዘኖቹ ገዝቶ ያከማቻቸውን የተለያዩ የምርጫ ቁሳቁሶችን በኤግዚቪሽን ማዕከልና በቦሌ ጉምሩክ መጋዘኖቹ ለጋዜጠኞች እያስጎበኘ ነው።
ቦርዱ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ ምርጫዎች በተለየ ምርጫን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማካሄድ የሚያስችል የምርጫ ቁሳቁሶች ግዢ ማድረጉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ሲተገበር የነበረው የምርጫ ሂደት እና ቀጣይ ሊደረግ የታቀደው የምርጫ ሂደት ቁሳቁስ ልዩነት ምን እንደሚመስል በማነፃፀርም የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲያዩ እየተደረገ ነው።
የአገር አቀፍ ምርጫ ኦፕሬሽን ዝግጅቶች

Source: NEBE
- የምርጫ ጣቢያ ብዛት - 50,900
- የሚጠበቁ መራጮች ቁጥር - 50,000,000
የአስፈጻሚዎች ቁጥር
- ለመራጮች ምዝገባ - 152,700
- ለድምፅ መስጫ ቀን - 254,500
ለመራጮች ምዝገባ የተዘጋጁ ቁሳቁሶች
- በአምስት ቋንቋዎች የተዘጋጁ የመራጮች መዝገቦች - 50,900 ጥራዞች
ለስልጠና የሚውሉ ሕትመቶች (በአምስት ቋንቋዎች የተዘጋጁ) - 8,200
የድምፅ መስጫ ቀን ቁሳቁሶች
- በግልጽ የሚያሳዩ የድምፅ መስጫ ሳጥኖች (በአንድ ጣቢያ አራት የድምፅ መስጫ ሳጥን ድረስ) - 207,000
- የምስጢር ድምፅ መስጫ መከለያዎች - 156,600
- ማስፈጸሚያ ቁሳቁስ የያዙ ሰማያዊ ሳጥን - 50,900
- መከፈታቸውን የሚያሳውቁ ቦርሳዎች - 712,600
- የጠረጴዛ ባትሪዎች - 110,800
መጪው አገር አቀፍ ምርጫ ኮቪድ -19ን ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን እንደሚያሟላ ቦርዱ አስታውቋል።