የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛውን አገር አቀፍ የመጨረሻ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ከዚህ ቀደም ታኅሣሥ 16 ቀን 2013 ዓ.ም የቦርዱ አመራሮችና ፖለቲካ ፓርቲዎች በተገኙበት የመጪው አገር አቀፍ ምርጫን ጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ለውይይት አቅርቦ ነበር።
በወቅቱ በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አቅርበው፣ ቦርዱ እጩዎችን ለማቅረብ የሚያስፈልገውን ፊርማ የሕግ መስፈርት ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ ብቻ አገልግሎት ላይ እንዳይውል የተወካዮች ምክር ቤትን ጠይቆ እንደነበር ይታወሳል።
ምርጫ ቦርድ ትናንት አመሻሽ ላይ የመጨረሻው ያለውን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።
ቦርዱ ለ ኤስ ቢ ኤስ በላከው የኢሜል መግለጫ እንዳረጋገጠው የተግባራቱን አፈጻጸም ሰሌዳ ይፋ ያደረገ ሲሆን ወደፊትም ያሉበትን ሁኔታ እንደሚያሳውቅ አስታውቋል።

Source: NEBE
የመጨረሻ ባለው የጊዜ ሰሌዳ ባለፈው በምክክሩ ወቅት ከገለፀው የተለየ ማሻሻያ ያላደረገ ሲሆን ምርጫው ግንቦት 28/2013 ዓም የሚካሄድ ይሆናል።
[ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ]