SKIP TO MAIN CONTENT

አምስት ፓርቲዎች የምርጫ ምልክቶቻቸውን እንዲቀይሩ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ

*** እስከአሁን 45 ያህል የፖለቲካ ፓርቲዎች ምልክቶቻቸውን አስገብተዋል

NEBE
Birtukan Mideksa, Chairperson of the National Election Board of Ethiopia. Source: Getty

2 min read

Published

By Stringer Report


Skip to article content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የፓርቲዎች የምርጫ ምልክት መረጣ እየተከናወነ ይገኛል።

እስከአሁን ድረስ 45 ያህል ፓርቲዎች ምልክቶቻቸውን ማስገባታቸውን ታውቋል።

የሚከተሉት ፓርቲዎች የመረጧቸው ምልክቶች በተለያዩ ምክንያቶች ቀይረው እንዲያቀርቡ ጥሪ እንደተደረገላቸው ቦርዱ አሳውቋል ፦

1ኛ. የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ - የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ

2ኛ. የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ- የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ

3ኛ. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) - የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ

4ኛ. የምዕራብ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በሆኑ

5ኛ. የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያቂ ንቅናቄ- ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በመሆኑ

 6ኛ. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) - ህጋዊ ሃላፊነት በተሰጠው አካል ምልክታቸውን እንዲመርጡ የተጠየቁ (በዚህም መሰረት የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የምርጫ ምልክት አስገብተዋል።) 

የምርጫ ምልክት ያላስገቡ፣ እንዲቀይሩ የተገለፀላቸው ወይም መቀየር የሚፈልጉ እስከ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንዲያጠናቁ ቦርዱ አሳስቧል።

የጸደቁ ምልክቶችን እና የፓርቲዎች ዝርዝር ሂደቱ ሲጠናቀቅ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ገልጿል።

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now