በኢትዮጵያ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ያለው ውጥረት እየከረረ በመጣበት ወቅት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እየተሰደዱ ነው

Ethiopian military gathered on a road near the border of the Tigray and Amhara regions.

Ethiopian military gathered on a road near the border of the Tigray and Amhara regions. Source: AAP

በኢትዮጵያ መንግስት የተቀመጠው የ72 ሰአታት የጊዜ ገደብ ወደማለቂያው በተቃረበበት ሰአት የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የመጀመሪያውን ውይይትን  በዝግ አድርጓል፡፡ይሁን እና ውይይቱን የአውርፓ እና የአፍሪካ ተውካዮች እንዳልደገፉት ተገልጿል ፡፡

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሀይል ታንኮቹ የመቀሌ ከተማን በ 60 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ዙሪያ መክበቡን አስታውቋል ፡፡ ገደቡ ከተጠናቀቀ በኋላ ለህወሀት የጦር ሀይሎች “ ምንም አይነት ምህረት እንደማያደርግ ” ቀደም ሲል ማስታወቁ ይታወሳል ፡፡  

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብባዊ መብቶች ክፍል ሀላፊ የሆኑት ማይክል ባችሌት ያደረባቸውን ስጋት በተመለከት ሲናገሩ “ በሁለቱም በኩል መቀሌ ላይ የሚታየው ከፍተኛ የሆነ ግብ ግብ ቀድሞውኑ ተጋላጭ እና በፍርሀት ውስጥ ባሉት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ታላቅ አደጋ ጥሏል ፡፡” ብለዋል

የአለማቀፉ የሰብአዊ ተሟጋቾች ድርጅት በበኩሉ ኢትዮጵያ ከባድ መሳሪያዎችን እና የአየር ጥቃትን እንዳትጠቀም ጥሪ አቅርቧል ፡፡ አያይዞ ሁለቱም ቡድኖች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎችንና  ከሌሎች አካባቢ ጥገኝነት ለመጠየቅ የመጡትን ሰዎች ደህንነት ጭምር ከግምት ውስጥ እንዲያስቡ አሳስቧል ፡፡

ሆን ተብሎ በሰላማው ሰዎች እና በሚጠቀሙባቸው ቦታዎች ላይ አደጋን መክፈት በአለማቀፉ የሰብአዊ መብቶች ህግ የተከልከለ እና በጦር ወንጀል መጠይቅንም እንደሚያስከትል ያሳሰቡት የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ የሰብአዊ ተሟጋቾች ድርጅት ሀላፊ ዴፕሮሳ ሙቼና ናቸው፡፡

እንደ መንግስት አባባል ከሆነ የ72 ሰአቱ ገደብ ይፋ ከሆነ ጀምሮ  ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ሚሊሻ እና ልዩ ሀይል አባላት ተከበዋል ፡፡

ህወሃት በበኩሉ ባለፈው ሰኞ ባደረገው ውጊያ በሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮችን እንደደመሰሰ እና በባህር ዳር ለፈጸመውም የሮኬት ጥቃት ሃላፊነትን ወስዷል ፡፡የትግራይ ክልል ያለ ምንም አይነት መገናኛ አማራጭ የቀረች በመሆኗ  ከሁለቱም በኩል የሚወጡትን መረጃዎች ከገለልተኛ አካላት ለማረጋገጥ አልተቻለም ፡፡

“ ግጭቱን ማብቃት ”

ህወሀት የአገር መከላከያ ወታደሮችን እና ካምፖችን በተቀነባበር ሁኔታ ካጠቃ በኋላ አጸፋውን ለመመለስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥቅምት 25 ወታደሮችን ፤ታንኮችን እና ተዋጊ አውሮፕላኖችን ካሰማሩ በኋላ ከተለያዮ አቅጣጫዎች የቀረቡላቸን የማሸማገል ጥያቄውዎች ሳይቀበሉ ቀርተዋል ፡፡

በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ዋና ጽህፈት ቤቱን ያደረገው የአፍሪካ ህብረት ፤ የቀድሞውን ፕሬዝደንት በልዩ ውክንና በትግራይ ውስጥ ላለው ቀውስ ለመውያየት ልኳል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ እንዳስታወቀው መግስት ለህብረቱ ያለውን ከበሬታ ለማሳየት ልኡኩን ተቀብሎ የሚያነጋግር ቢሆንም ከህወሀት ጋር ግን የሚደረግ ምንም አይነት ድርድር እንደማይኖር አስታውቋል ፡፡   

በትግራይ ያለው ቀውስ እየተባባሰ በመጣበት ወቅት ከ40000 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሱዳን ተሰደዋል ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ለምክክር በዙም  ቢቀመጥም ፤ በርካታ የአፍሪካ አገራት ውይይቱን ጥለው በመውጣታቸው በአጭሩ ያለመፍትሄ ተጥናቅቋል፡፡

በአንጣጻሩ የፈረንንሳይ ፤ የእንግሊዝ ፤ የቤልጂየም ፤የጀርመን እና ኢስቶንያ ዲፕሎማቶች አሜሪካን በመደገፍ ውይይቱ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በትናንትናው እለት ባወጣው መረጃ ጥቅምት 28 በማይ-ካድራ ከተማ በተደረገ ጭፍጫፋ ቢያንስ 600 የሚሆኑ ሰዎች  ህይወታቸውን ማጣታቸውን  አስታውቋል ፡፡    

   


Share

Published

Updated

By NACA
Presented by Martha Tsegaw

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
በኢትዮጵያ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ያለው ውጥረት እየከረረ በመጣበት ወቅት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እየተሰደዱ ነው | SBS Amharic