የሌበርና ሊብራል - ናሽናልስ ፓርቲዎች በዛሬው ዕለት ለ1.65 ሚሊየን የኩዊንስላንድ ስቴት መራጮች የወደፊት ራዕዮቻቸውን ገልጠዋል።
በሌበር በኩል ለኩዊንስላንድ መራጮች፤
- የኮሮናቫይረስ ወረርሽኙን ተቋቁመናል
- በወረርሽኙ የተጎዳው ምጣኔ ኃብት እንዲያገግም ፍኖተ ካርታ ዘርግተን ግብር ላይ ማዋል ጀምረናል
- በሺህዎች የሚቆጠሩ መምህራን፣ ሐኪሞች፣ ነርሶችና የፖሊስ ሠራዊት አባላትን እንቀጥራለን
- ዕድሜያቸው ከ25 በታች ለሆኑ ሁሉ ነፃ የTAFE ኮሌጅ ትምህርት እንሰጣለን
- ስለሆነም ለተቃዋሚ ቡድኑ ቀውስ ራሳችሁን ተጋላጭ ሳታደርጉ በሰከነና የረጋ አስተዳደር ቀጥሉ ሲል
የሊብራል - ናሽናልስ ፓርቲ በበኩሉ፤
- በወንጀል ላይ ጥብቅ እንሆናለን
- ወንጀልን ለመቀነስ ጊዜያዊ የሰዓት ዕላፊ ገደብ Townsville እና Cairns ላይ እንጥላለን
- የ$300 የመኪና ምዝገባ ተመላሽ እንሰጣለን
- የመብራት ወጪን ለመደገፍ ለንግድ ተቋማት ድጎማ እናደርጋለን
- ሆስፒታልና መንገዶችን እናድሳለን
በማለት በሌበር ምትክ እኔን ምረጡኝ ሲል ለመራጮች ጥሪውን አቅርቧል።