ታዳሽ ኃይል - የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኃይል አቅርቦት

*** ዓለም ለታዳሽ ኃይል አቅርቦት ትኩረት የሚሰጥበት ጊዜ ላይ እንደሚገኝ በአሜሪካ የታዳሽና ዘላቂ ሀይል ጥናት ተቋም ረዳት ዳይሬክተር ጄፍ ሎጋን አሳሰቡ

Wind turbines

Wind turbines stand in the light of the rising sun in the Harz foreland. Source: Getty

 በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ አራት የሀይል አጠቃቀም ሽግግር ምዕራፎች መታለፉን ረዳት ዳሬክተሩ ያስታውሳሉ፡፡ የመጀመሪያው የሰው ልጅ እሳትን መጠቀም የጀመረበት ጊዜ ሲሆን በዚህም እሳትን ለምግብ መስሪያ፣ ለሙቀት፣ ለማታ ብርሃንና ሌሎች አገልግሎቶች በመጠቀም የሰው ልጅ አእምሮውን እድገት ከፍ ማድረግ የቻለበት ነበር፡፡ ሁለተኛው ምዕራፍ የግብርና ምርት የጀመረበት ጊዜ ነው፤ ሶስተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ዘመን ሲሆን አራተኛው የሀይል አጠቃቀም ሽግግር ምዕራፍ ደግሞ አሁን በምንገኝበት ዓለም ከነዳጅና ከሰል ወደ ታዳሽ ዘርፍ እየተደረገ ያለው ሽግግር ነው ብለዋል፡፡

በዘርፉ የ30 ዓመታት ልምድና እውቀት ያካበቱት ጄፍ ሎጋን በቀጣይ ከከሰልና ከነዳጅ የሚገኘው የሀይል አቅርቦት በተለያዩ ምክንያቶች ተፈላጊነቱ እየቀነሰ እንደሚሄድ ገልፀዋል።

የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ፍቱን መዳህኒት የሆነው የታዳሽ ሀይል በየትኛውም የዓለም ክፍል በቀላል ወጪ ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል ተናግረዋል።

በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ብቻ ከአጠቃላይ የሀይል አቅርቦት 23 ከመቶ የሚሆነው ከጸሀይ ሀይል የሚገኝ ሲሆን በቴክሳስ ግዛትም ተመሳሳይ መጠን ያለው የኤሌክትሪክ ሀይል የሚገኘው ከነፋስ ነው፡፡
LADWPs Pine Tree Wind Farm
LADWPs Pine Tree Wind Farm and Solar Power Plant in the Tehachapi Mountains Tehachapi Mountains in Kern County, CA. Source: Getty
የ21ኛው መቶ ክፍለዘመን የሀይል አቅርቦት ትብብር ታዳሽ ሀይል ላይ መስራትን እንደሚያበረታታ የሚገልጹት የአሜሪካ የታዳሽና ዘላቂ ሀይል ጥናት ተቋም ረዳት ዳሬክተሩ ጄፍ ሎጋን ይህም አምራች ኩባንያዎችን ለውድድር እየጋበዘ እንደሚሄድ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጭንቀት ውስጥ የሚገኙት የዓለም ህዝቦች ከታዳሽ ሀይል ለሚገኝ ኤሌክትሪክ ቅድሚያ ሰጥተው ተጠቃሚ ይሆናሉ ነው ሚሉት፡፡

በመላው ዓለም በተሰሩ ጥናቶች ከታዳሽ ሀይል የሚገኘው የኤሌክትሪክ ዋጋ እየቀነሰ መጥቷል።

በዚህም በፈረንጆቹ 2024 አብዛኛው የታዳሽ ሀይል አቅርቦት ከነፋስና ከፀሀይ የሚገኝ እንደሚሆን ይገመታል ብለዋል።

ተሽከርካሪዎች ነዳጅን ከመጠቀም ይልቅ ታዳሽ ኤሌክትሪክን ወደመጠቀም እንደሚገቡም ባለሙያው ጥናቶችን ጠቅሰው ይተነብያሉ።

ለአብነት ቻይና እ.አ.እ በ2040 ከአጠቃላይ ተሽከርካሪዎቿ 70 ከመቶ የሚሆኑት የታዳሽ ሀይል ኤሌክትሪክን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ በጥናት መረጋገጡን ነው የተናገሩት።
A charging station
A charging station on a parking lot in a hazy day. Tianjin, China. Source: Getty
ከተለያዩ የዓለማት ክፍል ከተውጣጡ የአካባቢ ጥበቃ ዘጋቢ ጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ጄፍ ሎጋን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎች ፍላጎትን በተለይ ታዳጊ አገራት እንዴት ሊያሳኩ ይችላሉ ተብለው ለተጠየቁት ምላሽ ሲሰጡ "ሀገራት መኪኖችን ከውጭ ከማስገባት ይልቅ ወደማምረት እንደሚሸጋገሩ" ያላቸውን እምነት ገለፀዋል፡፡

በአሁኑ ውቅት ነዳጅና ከሰል የሚያመርቱና የሚያቀርቡ ተዋናዮች ለታዳሽ ሀይል ምን አይነት አመለካከት ይኖራቸዋል የሚለው ሌላው የተነሳ ጥያቄ ነው፡፡ በእርግጥ እስካሁን የነበሩ ተዋናዮች በታዳሽ ሀይል ጉዳይ ጥርጣሬ ቢያሳዩም ቢቲ እና ሼል ን የመሰሉ ካምፓኒዎች በታዳሽ ሀይል ዘርፍ አርአያ መሆን የሚችል እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የታዳሽ ሀይል በነዳጅና ከሰል አምራቾች ላይ ስለሚያሳድረው ተጽዕኖውም ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር፡፡ ጄፍ ሎጋን ሲመልሱም ሳውዲ አረቢያን መሰል የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የህዝብ ቁጥራቸው እየበዛ በመሆኑ ነዳጃቸውን ለህዝባቸው ከማዋል ይልቅ በታዳሽ ኃይል ኤሌክትሪክ እያቀረቡ ነዳጃቸውን  ለውጭ ገበያ እንደሚያውሉ ነው እምነታቸውን የገለጹት፡፡

በታዳሽ ሀይል ምርትና መልሶ ጥቅም ችግሮች ላይ ለተነሳው ጥያቄ የአሜሪካ ብሄራዊ የታዳሽ ሀይል ላብራቶሪ ባትሪና መሰል እቃዎችን መልሶ መጠቀም የሚያስችል ዲዛይን ለመስራት እየሞከረ ነው ብለዋል፡፡

ከጸሀይ የሚገኝ ሀይል ዋጋ ውድነትን በተመለከተ ከናይጀሪያ ተጠይቀዋል፡፡ ለዚህ መፍትሄው የዘርፉ ተዋናዮችን አፈጻጸም መሰረት ያደረገ መመሪያ አውጥቶ መተግበር ነው ብለዋል፡፡

ስለኒኩሌር ሀይል ቀጣይ እጣፈንታ የተጠየቁት ረዳት ዳሬክተሩ ይህ እንደየሀገራቱ ሁኔታ እንደሚወሰንና ዋናው ነገር ኒኩሌርን በጥንቃቄ መጠቀሙ ላይ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በአሜሪካ 20 ከመቶ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት ከኒኩሌር ሀይል እንደሚገኝ ያስታወሱት ጄፍ ሎጋን ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ሀገራቸው ለኒኩሌር ግንባታ የተለየ ትኩረት እንደሌላት ነው የተናገሩት፡፡

እንደብራዚል ያሉ ታዳሽ ሀይልና ነዳጅ ሀብት ያላቸው ሀገሮች ተግዳሮት አማዞንን ለመሰሉ ውድ ሀብቶች የሚሰጡት ጥንቃቄ እና በዋናነት በብራዚል ደግሞ የፓለቲካ አለመረጋጋት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሀይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የሚፈጸመው የሳይበር ጥቃት አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉ እንደማይቀር የተናገሩት በአሜሪካ የታዳሽና ዘላቂ ሀይል ጥናት ተቋም ረዳት ዳሬክተር ጄፍ ሎጋን ሀገራት ለዚህ ልዩ ትኩረት መስጠት አለባቸው ብለዋል፡፡

[ደመቀ ከበደ ]


Share

Published

By Demeke Kebede

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service