እንኳን ደስ ያለን፣ ዓባይ ከቤት ዋለ! - ኢሕአፓ

አዲሱ ትውልድ ይህን የአገር ሃብት የሆነውን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንዲንከባከበውና የትውልዱ የአድዋ ድል ተምሳሌት እንደሆነ ጠንቅቆ እንዲያጤን ከልብ እንመክራለን።

EPRP

Source: Courtesy of PD

አገራችን ኢትዮጵያ ብዙ የተፈጥሮ ሃብት በውስጧ አምቃ የያዘች አገር ናት። ይሁን እንጂ የተለያዩ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በፈጠሩት ተግዳሮቶች ምክንያት ዕምቅ ሃብቷን በበቂ መጠቀም ያልቻለች አገር መሆኗ ደግሞ እሙን ነው። ከነዚህ እምቅ የተፈጥሮ ሃብቶቿ አንዱ የዓባይ ውሃ ነው። ዓባይ የኢትዮጵያን ለም አፈር ተሸክሞ አገር አቋርጦ በመጓዝ የታችኛው ተፋሰስ አገሮችን ሲመግብ መኖሩ ይታወቃል።

እነዚህ ጎረቤት ተፋሰስ አገሮች የዓባይን ውሃ በመጠቀም ዘመናዊ እርሻና የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት አገራቸውን በከፍተኛ ደረጃ አበልጽገዋል። ያለማንም ጠያቂ ግድብም ገድበው እየተጠቀሙ ይገኛሉ። ግብፆች ወደ ሃገራቸው የሚፈሰውን 86% ውሃና ተሸክሞት የሚነጉደውን ለም አፈር በረከት የሚሰጣቸው ጥቁር ዓባይ የሚመጣው ከኢትዮጵያ መሆኑን በትክክል ያውቃሉ።

ይሁን እንጂ የውሃው ባለቤት እኛ እንጂ ኢትዮጵያ አይደለችም በማለት በዓለም መድረክ ላይ ከግብረአበሮቻቸው ጋር በመሆን የዓለምን ሕዝብ ለማሳመን ከፍተኛ የገንዝብና የሰው ኃይል መድበው ሲዘምቱብን ኖረዋል። ለልጆቻቸውም ዓባይ መነሻውም ግብፅ ውስጥ፣ መድረሻውም ግብፅ እንደሆነ አድርገው የተሳሳተ ትርክትን ሲያስተምሯቸው ኖረዋል።

ግብፅ ያመቸኛል ባለችበት ጊዜም ዓባይን ከምንጩ ለመቆጣጠርና ኢትዮጵያን አዳክማ ወይም አጥፍታ ለመግዛት በተለያዩ ጊዜያት ወታደር አዝምታ፣ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ከፍታ ነበር። ነገር ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ የአገሩ ዳር ድንበር ሲነካበት ቀፎው እንደተነካበት ንብ በአንድ ላይ ተነስቶ እንዳመጣጧ በተደጋጋሚ አሳፍሮ መልሷታል።

ግብፅ ኢትዮጵያ የሌለችበትን የቅኝ ግዛት የውሃ ክፍፍል ውል አገራችን እንድትቀበል ለማድረግ ከፍተኛ ወጭ በማውጣት ይኽው እስካሁን ትሞግታለች። ይህንኑ ለማሳካት በዲፕሎማሲው ረገድም የማትፈነቅለው ድንጋይ የላትም። አገሯን በእርሻና በመብራት ኃይል ስታለማ ኢትዮጵያ ግን በተደጋጋሚ በከፍተኛ ድርቅና ረሃብ ትጠቃለች።

አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠጣ ንጹህ ውሃና የኤሌክትሪክ መብራት የለውም። እነዚህ አገልግሎቶች አሉ በሚባሉባቸው ቦታዎችም በበቂ ባለመኖራቸው የሀገሪቱን የመልማት አቅም እንዲቀጭጭና ሕዝቧም በንጹህ የመጠጥ ውሃ እጦት በበሽታ እንዲሰቃይ ሆኗል። ይህን ችግር ለመቅረፍ ኢትዮጵያ ታላቁን የዓባይ ግድብ መሥራት ከወጠነችበት ጊዜ ጀምሮ ግብፅ አንዳንዴም ከሱዳን ጋር በመተባበር ግድቡ እንዳይሠራ ከፍተኛ እንቅፋት ስትፈጥር ቆይታለች።

የዓለም አቀፍ የገንዝብ ተቋማት ለግድቡ ማሠሪያ የሚውል ገንዝብ እንዳያበድሩ ከመከላከል አልፋ ጦርነት እከፍታለሁ እስከ በማለት እስካሁኑ ሰዓት ድረስ ትዝታለች። የተለያዩ እንቀፋቶችንም ስተደረድር ይታያል።

ሀገራችን ይህን ሁሉ ዘመቻ ተቋቁማ ያለምንም የውጭ ብድር በኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዝብ እየተገነባ ያለው ግድብ የመጀመሪያውን የውሃ ሙሌት መጀመሩን የተቀበልነው በከፍተኛ ኩራትና ደስታ ነው። ከዕለት ጉርሱ እየቀነሰ ገንዝቡን በማዋጣትና ቦንድ በመግዛት “ዓባይ የኔ ነው” ብሎ በቆራጥነት እየተሳተፈ ያለውን የኢትዮጵያን ሕዝብ፣ ኢሕአፓ ከልብ ያመሰግናል።

ግድቡን በመሥራት- በሥራ አስኪያጅነት፤ በሞያተኝነት፤ በተደራዳሪነትና በዜጋ ዲፕሎማትነትና በሌሎችም መስኮች ሁሉ የዜግነት ግዴታቸውን ለተወጡና ለተባበሩ ኢትዮጰያውያን ሁሉ ኢሕአፓ አድናቆቱን ይገልፃል።
ከዕለት ጉርሱ እየቀነሰ ገንዝቡን በማዋጣትና ቦንድ በመግዛት “ዓባይ የኔ ነው” ብሎ በቆራጥነት እየተሳተፈ ያለውን የኢትዮጵያን ሕዝብ፣ ኢሕአፓ ከልብ ያመሰግናል።
ሥራው ተገባደደ እንጂ አላለቀም፣ በመሆኑም ፓርቲያችን ከሕዝባችን ጋር በመሆን የግድቡ ሥራ እንዲጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ያረጋግጣል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሥራው መጠናቀቁ ብቻ ሳይሆን ከዚያ ባሻገር የግድቡ ዘላቂ ደህንነት መረጋገጥና ተጓዳኝ የልማት ሥራዎችን መሥራት እንዲቻል ሁላችንም በጋራ ሆነን፣ ያለምንም መታከት፣ ከፍተኛ ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልገን ኢሕአፓ ለማሳሰብ ይወዳል።

የዓለም የውሃ ተፋሰስ አገሮች ሕግ በሚያዘው መሠረት ኢትዮጵያ የታችኛው ተፋሰስ አገሮችን በማይጎዳ መንገድ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት መርኅ ባደረገ መንገድ የምታደርገውን ድርድር የምንደግፍ መሆናችን በድጋሚ እንገልጻለን። የአገራቸውን ጥቅም ለሥልጣንና ለገንዘብ ብለው አሳልፈው ለመስጠት ሽር ጉድ የሚሉትን አገር በቀል ግለሰቦችንም ሆነ ድርጅቶች ወደቀልባቸው እንዲመለሱ ልናሳስባችው አልፎም ልንታገላቸው ይገባል።

ግብፅ አገራችን ያላትን የውሃ አቅም የመጠቀምና የመልማት ተፈጠሯዊ መብት ለመንፈግ የምታደርገውን ዛቻ ኢሕአፓ አጥብቆ ያወግዛል። ከሕዝባችን ጎን ቆመን ልንታገላትም መቁረጣችን እንዲታውቅ ያስፈልጋል። ከአገር ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን የአገራችን መብት ላለማስደፈር የሚያደርጉትን የቴክኒክ፣ የዲፐሎማሲና የቈሳቁስ ርብርብ እጠናክረው እንዲቀጥሉ ከልብ እናበረታታለን።
ግብፅ አገራችን ያላትን የውሃ አቅም የመጠቀምና የመልማት ተፈጠሯዊ መብት ለመንፈግ የምታደርገውን ዛቻ ኢሕአፓ አጥብቆ ያወግዛል።
አዲሱ ትውልድ ይህን የአገር ሃብት የሆነውን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንዲንከባከበውና የትውልዱ የአድዋ ድል ተምሳሌት እንደሆነ ጠንቅቆ እንዲያጤን ከልብ እንመክራለን። የተፎካካሪ ፓርቲዎችም የአገራችንን ብሄራዊ ደህንነት ከሕዝባችን ጋር ቁመን በጋራ እንድንጠብቀው፣ ለአባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን እንድናስተምር በዚህ አጋጣሚ ኢሕአፓ ጥሪውን ያቀርባል።
አዲሱ ትውልድ ይህን የአገር ሃብት የሆነውን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንዲንከባከበውና የትውልዱ የአድዋ ድል ተምሳሌት እንደሆነ ጠንቅቆ እንዲያጤን ከልብ እንመክራለን።
እንኳን ደስ ያለን! ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ

ሐምሌ 23 ቀን 2012 ዓ. ም

አዲስ አበባ


Share

Published

Updated


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
እንኳን ደስ ያለን፣ ዓባይ ከቤት ዋለ! - ኢሕአፓ | SBS Amharic