ካማላ ሃሪስ የዲሞክራት ፓርቲ ዕጩ ምክትል ፕሬዚደንት ሆኑ

የዲሞክራት ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ለኖቬምበሩ ምርጫ ሴናተር ካማላ ሃሪስን ምክትላቸው ሆነው እንዲወዳደሩ መረጡ።

Kamala Harris

Sen. Kamala Harris Source: US Senator Kamala Harris addresses supporters during her own presidential campaign in 2019.

የዲሞክራት ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ለዘንድሮው የኖቬምበር ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የቀድሞ ተቀናቃኛቸውን ሴናተር ካማላ ሃሪስን ምክትላቸው ሆነው እንዲወዳደሩ መርጠዋቸዋል።
Kamala Harris
Source: Courtesy of JB
Kamala Harris
Joe Biden and Kamala Harris Source: Courtesy of KH
ሴናተር ሃሪሰንም በበኩላቸው በዕጩ ፕሬዚደንት በመመረጣቸው ክብር የተሰማቸው መሆኑን፣ የበኩላቸውንም ለመወጣትና ለጆ ባይደን ሙሉዕ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጠዋል።
Kamala Harris
Source: Courtesy of KH
የ55 ዓመቷ ሴናተር ካማላ ከጃማይካዊ አባትና ሕንዳዊ እናት የተወለዱ ናቸው።
Kamala Harris
Shyamala Harris (mother) and baby Kamala Harris Source: Courtesy of KH
ሴናተር ሃሪስ October 20, 1964 የተወለዱት ኦክላንድ - ካሊፎርኒያ ነው።

አባታቸው ዶናልድ ሃሪስ የምጣኔ ሃብት ፕሮፌሰር ሲሆኑ እናታቸው ሻያማላ ጎፓላንድ የጡት ካንሰር ተመራማሪ ነበሩ።

እናትና አባታቸው ገና የአምስት ዓመት ልጅ ሳሉ የተለያዩ ሲሆን በ2009 በሞት ከተለዩዋቸው እናታቸው ጋር ሆነው አድገዋል።

ከሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የተመረቁት ሃሪሰን የካሊፎርኒያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሆነው በ2010 እና 2014 ለሁለት ተከታታይ ጊዜያት ተመርጠው አገልግለዋል።

በ2016 ካሊፎርኒያን በመወከል የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ሆነ በመመረጥ ሶስተኛዋ የካሊፎርኒያ ሴት ተመራጭ፣ ሁለተኛዋ የአፍሪካውያን - አሜሪካውያንና የመጀመሪያዋ የደቡብ-እስያ ዝርያ ያላቸው የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር ለመሆን በቅተዋል።

በ2020 የዲሞክራት ፓርቲን ወክለው ለዕጩ ፕሬዚደንትን ትወዳድረው ጆ ባይደን አሸናፊ ሆነው ተጠናቅቋል።

ሆኖም ትናንት ኦገስት 11 - 2020 ጆ ባይደን ምክትላቸው ሆነው አብረው ለ2020 ፕሬዚደንታዊ ምርጫ እንዲወዳደሩ መርጠዋቸዋል።

ከጄራሊዲን ፌራሮ እና ሳራ ፔሊን ቀጥሎ ሶስተኛዋ የዩናይትድ ስቴትስ ዕጩ ፕሬዚደንት በመሆነም የታሪክ ባሕር መዝገብ ውስጥ ራሳቸውን ለማኖር በቅተዋል። 
Kamala Harris
Kamala Harris (L), Sarah Palin (C) and Geralidine Ferraro (R) Source: Courtesy of WP
የካማላ ሃሪስ የዲሞክራት ፓርቲ ዕጩ ምክትል ፕሬዚደንትን አስመልክቶ የቀድሞ ፕሬዚደንቶች ባራክ ኦባማና ቢል ክሊንተን፤ የ2016 የዲሞክራት ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚደንት ሂላሪ ክሊንተንን ጨምሮ በርካታ የድጋፍ መልዕክቶች ተስተጋብተዋል።
Kamala Harris
Source: Courtesy of BO
Kamala Harris
Source: Courtesy of BC and HC



Share

Published

Updated

By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service