የዲሞክራቱ ጆ ባይደን የዩናይትድ ስቴትስ 46ኛው ፕሬዚደንት ሆነው በመመረጥ የሪፐብሊካኑን ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዚደንታዊ ዘመን በአራት ዓመት እንዲያከትም ማድረግ ችለዋል።
ለ77 ዓመቱ ጆ ባይደን ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ድል መረጋገጥ ሁነኛ አስተዋፅዖ ያበረከተው ፔንሲልቫኒያ 20 የምርጫ ኮሌጅ ድምፆችን ምርጫው ከተካሄደ አራት ቀናት ዘግይቶ በአውስትራሊያ ሰዓት አቆጣጠር ከእኩለ ቀን በኋላ አስቆጥሯል።
ኔቫዳም በበኩሏ ስድስት የምርጫ ኮሌጅ ድምፆችን ለጆ ባይደን በማስገኘት በጥቅሉ ለፕሬዚደንታዊ ምርጫ ግድ የሚለውን 270 የምርጫ ኮሌጅ ድምፅ በማለፍ 279 ድምፆችን እንዲያገኙ አስችላለች።
ሆኖም ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ውጤቱን በመቀበል እንኳን አደረሰዎት ብለው ለጆ ባይደን ስልክ ከመደወል ይልቅ ራሳቸውን በአሸናፊነትና የምርጫውንም ሂደት በመጭበርበር የታጀበ መሆኑን ገልጠዋል።
ከጆ ባይደን ጋር ተመራጭ የዩናይትድ ስቴት ምክትል ፕሬዚደንት የሆኑት ካማላ ሃሪስ የመጀመሪያዋ ሴትና ጥቁር ፕሬዚደንት ለመሆን በቅተዋል።
ለጆ ባይደንም የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የቀድሞው ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማም በበኩላቸው ለጆ ባይደን የእንኳን አደረስዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰንም ተመራጭ ፕሬዚደንት ጆ ባይደንን እንኳን ደስ ያለዎት ብለዋል።
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም በበኩላቸው ለጆ ባይደን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የቀድሞው የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ማልከም ተርንቡል በበኩላቸው ለጆ ባይደንና ካማላ ሃሪስ ምርጫ የተሰማቸውን እፎይታ ገልጠው የእንኳን ደሳላችሁ የግል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Donald J. Trump Source: DT

Kamala Harris Source: KH

Kamala Harris Source: KH

Barack Obama Source: BO

Scott Morrison Source: SM

Abiy Ahmed Source: AAA

Malcolm Turnbull Source: MT