ፕርምየር ዳንኤል አንድሪውስ የኮቪድ - 19 ወረርሽኙን ለማጥፋት ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገናል ስለሆነም ገደቡን ለሰባት ቀናት አራዝመናል ሲሉ ተነገሩ ።
በቪክቶርያ በማህበረሰብ ውስጥ እየተሰራጨ ያለው የኮቪድ - 19 ተያዦች ቁጥር በመጨመሩ ሳቢያ ተጥሎ የነበረው ገደብ ለተጨማሪ አንድ ሳምንት ተራዝሟል።
ፕርምየር ዳናኤል አንድሪውስ ያረጋገጡትም አምስት ቀን የነበረው ገደብ እስከ መጪው ማክሰኞ ጁላይ 27 ድረስ መራዘሙን ነው።
“ ጊዜ እንፈልጋለን በከፈተኛ የጤና ኦፊሰሮች ምክር ላይ በመመስረት ገደቡን ለተጨማሪ ሰባት ቀናት አረዝመነዋል ” ሲሉ ለሪፖርተሮች ተናግረዎል ።
“ ራሳችንን ለአደጋ ማጋለጥ አንፈልግም የማናውቀው የቫይረስ ስርጭት አለ”
ቪክቶርያ 13 አዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎችን ቁጥር ያስመዘገበች ሲሆን እስከ ማክሰኞ ድረስ ባለው መረጃ መሰረትም 50,000 የሚሆኑ ሰዎች የኮቪድ - 19 ምርመራን አድርገዋል ።
በትናንትናው እላት የተመዘገበው 12 የተጠቂዎች ቁጥርም በአሁን ሰአት ካለው የዴልታ ቫርያንት ወረርሽኝ ጋር ተያያዝ ሲሆን ምንጩም ከኒው ሳውዝዊልስ ነው ። የአንደኛውን የቨይረስ ምንጭ ለማወቅ አሁንም በምርመራ ላይ ያለ ሲሆን የተቀሩት ዘጠኙ በለይቶ ማቆያ ይገኛሉ ።