የኮማንደር ለማ ጉተማ የውልደት ቀዬ በአርሲ ክፍለ አገር፣ ጭላሎ አውራጃ የምትገኘው በቆጂ ናት።
እግራቸው ሲጠና ለትምህርት ወደ አዲስ አበባ አቀኑ። የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውንም በኮከበ ፅባህ ትምህርት ቤት ፈጸሙ።
በ1951 የኢትዮጵያ ባሕር ኃይልን ኮሌጅ ዕጩ መኮንን ሆኑ። ስልጠናቸውንም ጨርሰው በላቀ ውጤት ተመረቁ። ሲልም፤ ወደ ባሕር ማዶ አቅንተው በአገረ እንግሊዝና ዩናይትድ ስቴስ የባሕር ኃይል መኮንን ወታደራዊ ዕውቀታቸውን ከፍ አድርገው ገነቡ።
ወደ አገር ቤት ከተመለሱም በኋላ በ1960 የቀደማዊ ኃይለ ሥላሴ የሕግ ፋክሊቲ ከመጀመሪያዎቹ የሕግ ተማሪዎች አንዱ ሆነው በመጀመሪያ ዲግሪ ለመመረቅ በቁ።

Lemma Gutema Source: Courtesy of SLG
ኮማንደር ለማ በውትድርና ሕይወታቸው በኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ኮሌጅ አስተምረዋል፤ በሕግ አማካሪነትና በቃኚ ጦር መርከብ አዛዥነት አገልግለዋል።
በሲቪል አስተዳደር በካሣ ኮሚሽን ኮሚሽነርነት፣ በሐረርጌ ክፍለ አገር አስተዳዳሪነትና በአገር አስተዳደር ሚኒስትርነት ሰርተዋል።
በዲፕሎማሲው ዘርፍ በጀርመን ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የኢሕዲሪ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ሰርተዋል።
በፖለቲካው ዘርፍም፤ በአዲስ አበባ የኢሠፓአኮና ኢሠፓ አንደኛ ጸሐፊ፤ ከፍ ብለውም ኢሕአዴግ የኢሕዲሪን መንግሥት እስከ ከላ ድረስ የኢሕዲሪ ሸንጎ ምክትል ፕሬዚደንት ነበሩ።

Lemma Gutema Source: Courtesy of SLG

Mengistu Hailemariam (L) and Lemma Gutema (R) Source: Courtesy of SLG
ከሰባት ዓመታት እስራት በኋላም በልብ ህመም ሳቢያ የካቲት 29 – 1990 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።