አገር ቤትና ባሕር ማዶ - “ሰው አገርም ብንሆን ለኢትዮጵያ መልካም ነገርን እንመኝ።” - አሰፋ በቀለ

Interview with Assefa Bekele

Assefa Bekele Source: Courtesy of AB

አቶ አሰፋ በቀለ ቤተሰባቸውን ጨምሮ ነዋሪነታቸው በሲድኒ - አውስትራሊያ ነው። አጭር ግለ-ታሪካቸውን ከትውልድ ቀዬአቸው ድሬ-ወሊሶ ጋር አጣቅሰው፤ የአገረ ግሪክ ቆይታና የአውስትራሊያ ሠፈራቸውን አያይዘው ያወጋሉ።


የአቶ አሰፋ እናት ገና በለጋ ዕድሜያቸው በአማጭ-ረማጭ ለጋብቻ በመዳረጋቸው ደስተኛ አልነበሩምና የመጀመሪያ ልጃቸውን ትንሹን አሰፋና ባለቤታቸውን ጥለው ወደ አዲስ አበባ ገብተው ነበር።

ጥቂት ቆይተው ግና ወደ ወሊሶ ተመልሰው የመጀመሪያ ልጃቸውን ትንሹን አሰፋ ይዘው ወደ አዲስ አበባ ዘለቁ። ይሁንና አዲስ አበባ የገጠሩን ልጅ አሰፋን ፈተነች፤ ችሮታዋንም ለገሰች። የግሪክ አገር የነጻ ትምህርት ዕድልን እነሆኝ አለች።

Interview with Assefa Bekle
Assefa Bekele Source: Courtesy of AB

ወደ ግሪክ አገር ሲሔዱ ትልማቸው ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ለማጥናት ነበር። ይሁንና በአባታቸው ግሪካዊ፣ በእናታቸው ኢትዮጵያዊ በሆኑ አንድ ግሪካዊ ፕሮፌሰር ምክረ ሃሳብ ሳቢያ በማዕድን ምሕንድስና በዲግሪ ተመረቁ። ሲልም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አገኙ።

ግሪክ የሙያ ስልጠና ብቻ ሳይሆን የሕይወት ተጋሪም አገጣጥማ ሰጥታቸዋለች። ዛሬም ድረስ ከአራት አሠርት ዓመታት በላይ አብረው በፍቅርና በትዳር በመኖር የልጅ ልጆች ድረስ በጋራ ለማየት ካበቋቸው ወይዘሮ ዓለም ጋርም የተገናኙት እዚያው ግሪክ ነው።

Interview with Assefa Bekle
Assefa Bekle and Alem Source: Courtesy of AB

ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ቁርስ ቀምሰው ምሳ ሳይበሉ ያደጉባት ብትሆንም፤ ዛሬም ድረስ “ታላቅና ወርቅ አገር” ብለው ነው የሚጠሯት። ምኞታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የተጀመረ የለውጥ ሂደት ለስኬት እንዲበቃ ነው።

Interview with Assefa Bekele
Assefa Bekele Source: Courtesy of AB

እርግጥ ነው፤ ከመላው ቤተሰባቸው ጋር ውለው ለሚገቡባት አውስትራሊያ ያላቸው ፍቅርም ብርቱ ነው።

Interview with Assefa Bekele
The family of Assefa Bekele Source: Courtesy of AB


Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service