የፕሮፌሰር ጌታቸው የግለ ታሪክ መነሻ የትውልድ ሥፍራቸው ሸንኮራ ናት። በምርጥ የስንዴ ምርቷ “እንውረድ ሸንኮራ፣ ስንዴ ልንበላ” የተባለላት።
አባታቸው ቀኛ አዝማች ኃይሌ ወልደየስ ከካህናት ወገን ሲሆኑ፤ እናታቸው ወይዘሮ አሰገደች ወልደዮሐንስ ከነፍጠኞች ወገን ናቸው። ኩሉኮንታ የመወለዳቸው፤ ወላይትኛና ኦሮሞኛ የመናገር ችሎታ ምስጢራቸውም ከውልደትና ዕድገታቸው ጋር መያያዙ ነው።
በወላጆቻቸው ከቀዬ ቀዬ መዘዋወርና መለያየት ሳቢያ የመኖሪያ አድራሻቸው ብዙ ጊዜ ተቀያይሯል። ከሸንኮራ ይልቅ ወደ አዲስ አበባ ዘልቀው የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረትና ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያናት ፊደል ተማሪ ሆነዋል።

ቀኝ አዝማች ኃይሌ ወልደየስ (ግራ) ወይዘሮ አሰገደች ወልደዮሐንስ (ቀኝ) - ፎቶ አንዳፍታ ላውጋችሁ - ጌታቸው ኃይሌ Source: Courtesy of Getachew Haile
ጥረትና ገዳቸው ተገጣጥመው በዓለማዊው ቀለምና በመንፈሳዊ ትምህርት ሊበለጽጉ ወደ ካይሮ አቀኑ። ከካይሮ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን (Bachelor of Divinity) አግኝተዋል።
የክፍል አንድ ትረካቸው የሚቋጨው እዚህ ላይ ነው። በቀጣዩ ክፍል ሁለት ዝግጅታችን የአውሮፓ የትምህርትና ግለ ሕይወት ታሪካቸውን ያወጉናል።

ጌታቸው ኃይሌ (ካይሮ መናፈሻ) Source: Courtesy of Getachew Haile





