አንኳሮች
- የመኖሪያ ቤት፣ የንግድ፣ የመኪናና የፕሮጄክቶች ብድር አሠራር
- የወለድ መጠኖች
- የባንክ ሂሳብ አከፋፈት
- የባንክ ሂሳብ ዓይነቶች
ዳያስፖራ ብለን የምናጠቃልላቸው ኢትዮጵያዊ ሆነው በውጭ የሚኖሩ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሆነው የተለያዩ ሀገራት ዜግነት ያላቸውንና በውጭ ሀገር አንድ ዓመትና ከእዚያ በላይ ኖረው የተመለሱትን ነው።አቶ ዘሪሁን ተከተል፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳያስፖራ ባንክ ክፍል ሥራ አስኪያጅ
በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን 'ሀገሬ ላይ ቤት ልግዛ ወይም ልሥራ ወይም የተጀመረ ቤት ልጨርስ' ብለው ለሚያስቡ፤ ዝቅተኛው 10 በመቶ የሆነ መዋጮ በማውጣት እስከ 20 ዓመት የሚቆይ ባለ ሶስት ዘርፍ ብድር ተዘጋጅቶላቸዋል።አቶ ዘሪሁን ተከተል፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳያስፖራ ባንክ ክፍል ሥራ አስኪያጅ
በውጭ ምንዛሪ በባንክ ሂሳብ የተቀመጠው፤ ሀገር ውስጥ በዶላር ወጪ አይደረግም። በብር ይቻላል። ለምን? ኢትዮጵያ ውስጥ የገንዘብ ዝውውር በብር ስለሆነ ነው። እሱን እናጥራ። ነገር ግን፤ ውጭ ሆነው በዶላር የገንዘብ ዝውውር ማድረግ የሚፈልጉ የእራሳቸውን የባንክ ሂሳብ በዶላር መጠቀም ይችላሉ።አቶ ዘሪሁን ተከተል፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳያስፖራ ባንክ ክፍል ሥራ አስኪያጅ
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት መካከል የተካሔደው የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ፤ አግልግሎቶችን ለዳያስፖራው ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ነው።አቶ ዘሪሁን ተከተል፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳያስፖራ ባንክ ክፍል ሥራ አስኪያጅ





