Herman Cohen, former US Assistant Secretary of State for African Affairs (L), and Yeharerwerk Gashaw (R) Source: Courtesy of YWG
የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ዓለም አቀፍ ሞዴል የሐረርወርቅ ጋሻው፤ በክፍል አንድ ግለ ሕይወት ትረካቸው ከትውልድ ቀዬአቸው ቀላዳንባ-ሐረር ተነስተው አሁን መኖሪያ አድረገዋት ወዳለችው አገረ አሜሪካ እንደምን ጠቅልለው እንደሠፈሩ ነግረውናል። በሂደቱም ወደ ሞዴልነት ሙያ እንዴትና መቼ እንደተሰማሩም ነቅሰው አውግተውናል። የማጠቃለያ ክፍል ሁለት ትረካቸው የሚጀምረው ዓለም አቀፍ የሞዴልነቱ ሚና ያላበሳቸውን ሞገስ እንደምን ለፖለቲካዊ፣ ሰብዓዊና ምግባረ ሰናይ ጉዳዮች እንዳዋሉት ነው።
የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ዓለም አቀፍ ሞዴል የሐረርወርቅ ጋሻው፤ በክፍል አንድ ግለ ሕይወት ትረካቸው ከትውልድ ቀዬአቸው ቀላዳንባ-ሐረር ተነስተው አሁን መኖሪያ አድረገዋት ወዳለችው አገረ አሜሪካ እንደምን ጠቅልለው እንደሠፈሩ ነግረውናል። በሂደቱም ወደ ሞዴልነት ሙያ እንዴትና መቼ እንደተሰማሩም ነቅሰው አውግተውናል። የማጠቃለያ ክፍል ሁለት ትረካቸው የሚጀምረው ዓለም አቀፍ የሞዴልነቱ ሚና ያላበሳቸውን ሞገስ እንደምን ለፖለቲካዊ፣ ሰብዓዊና ምግባረ ሰናይ ጉዳዮች እንዳዋሉት ነው። ለረድዔት ተግባር ወደ ኢትዮጵያ ዘልቀው ሕይወታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለፈው የአሜሪካ የምክር ቤት አባል ሚኪ ሊላንድ ግብር የላቀ ከበሬታ እንዲያገኝ ጥረዋል። ስኬትም ገጥሟቸዋል።
Mickey Leland's Children Home in Addis Ababa, August 4, 1990 Source: Courtesy of public domain በወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት የነበሩት መንግሥቱ ኃይለማርያም ሳይቀሩ ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል።
The Ethiopian Actress and Model meets with Ethiopian President Mengistu H.Mariam in order for the president to honor Mickey Leland. Source: Ethiopian Press in 1990 የፓን-አፍሪካኒዝም ዓላማ አራማጅ እንደመሆናቸውም ከአፍሪካውያን መሪዎች ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።
Human rights advocate Yeharerwerk Gashaw sharing with Mandela and Mobutu in Dallas, Texas Source: Courtesy of FK Yeharerwerk Gashaw met with Vice-President Augustaus Aikhomu on September 22, 1990 at the State House in Lagos Nigeria. Source: Courtesy of FK የመንግሥቱ ኃይለማርያም የአገዛዝ ሥርዓት በኢሕአዴግ አገዛዝ ሲተካና ኤርትራም ሉዓላዊት አገር ስትሆን፤ ኢትዮጵያውያን የጦር ምርኮኞችን ለማስፈታት ኤርትራ ድረስ ዘልቀው ከፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂና የጦር ምርኮኞች ጋር ተነጋግረዋል።
Yeharerwerk Gashaw with Ethiopian POWs Source: Courtesy of public አሁን በቅርቡም የኢትዮጵያ ጉዳይ በብርቱ አሳስቦኛል ብለው ተነስተው ከቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ከነበሩት ኽርማን ኮኸን ጋርም ‘ምን መደረግ አለበት?’ ሲሉ መክረዋል።
ሁሉን አቀፍ የሽግግር ሂደት እንዲፈጠር አሜሪካ ልዩ ሚና እንድትጫወት ምክረ ሃሳባቸውን ለኮኸን አቅርበዋል።