Minister Dagmawit Moges: How Can A Woman Succeed in Ethiopian Politics?

Dagmawit Moges: Ethiopian Woman in Politics

Dagmawit Moges Source: SBS Amharic

ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፤ ከሳምንት ዕድሜ በፊት ሐዋሳና አዲስ አበባ ላይ ስንገኛ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ነበሩ። ይትባሃሉ ‘በፖለቲካ ዓለም አንድ ሳምንት ረጅም ጊዜ ነው’ እንዲል፤ ሰሞኑን የትራንስፖርት ሚኒስትርና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የካቢኔ አባል ሆነዋል።በችሮታ ሳይሆን በምዘና።


 የመሪነት ዕሳቤ ውስጣቸው የሰረጸው ገና ለጋ ወጣት ሳሉ ነው።የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ሆነው የተማሪዎች ማኅበር አቁመው የመጀመሪያዋ ፕሬዚደንት ሆነዋል።

“መሪነት በችሮታ አይሰጥም፤ የሚወሰድ ነው።” ብለው ያምናሉ።
“መሪነት በችሮታ አይሰጥም፤ የሚወሰድ ነው።”
የልጅነት ሕልማቸው የአመራር ወንበራቸውን ፒያሳ ህንፃ ላይ ማድረግ ነበር። የፒያሳ ሰማይ ጠቀስ ህንፃ ከሰሞነኛ ርዕሰ ዜናነት ሳያልፍ ቀረና ያ አልሆነም።
Dagmawit
Dagmawit Moges Source: SBS Amharic
ግና ብዙም ሳይርቁ፤ ትንሽ ፈንጠር ብለው የመጀመሪያዋ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴት ምክትል ከንቲባ ሆነዋል። ቀን ቆርጠን የተነጋገርነውም እዚያው የማዘጋጃ ቤቱ ቢሮአቸው ውስጥ ነው።
Dagmawit
Addis Ababa City Hall Source: SBS Amharic
የረፋዷ የአገር ቤት ጸሐይ ለቢሮአቸው ያለስስት ብርሃኗን ለግሳ ድምቀትን አላብሳላቸዋለች። የግድግዳው ክሪም ቀለም በጥንቃቄ ከተመረጠው የስጋጃ ምንጣፍና አገርኛ ትንቡኬ መቀመጫ ጋር ተስማምተው ክፍሉን ሞገስ አላብሰውታል። ጥጋቱ ላይ ዘለግ ብለው የወጡትና የጽህፈት ጠረጴዛቸው ፊት ለፊት ተዛንቀው የተቀመጡት ባለ ሕብረ ቀለማት አበቦች ተሰናስለው ቢሮውና ወንበሩ በእንስት የተያዙ መሆኑን ይመሰክራሉ። ውስጣዊ ስክነትን ያላብሳሉ።
Dagmawit
Dagmawit Moges Source: SBS Amharic
ዳግማዊትም ነቃና ዘና እንዳሉ ነበር ስለ SBS የምስረታ ታሪክና አስተዋጽዖዎች፣ ዲሞክራሲ በአገረ አውስትራሊያ በግብር ላይ እንደምን እየዋለ እንዳለ አዋዝተን፤ የሐዋሳውን የኢሕአዴግ 11ኛ መደበኛ ጉባኤ በቅንጭቡ ነቅሰን፤ የኢትዮጵያውያን ሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ በእሳቸው ሕይወት ዙሪያ ቃኝተን ወደ ቃለ ምልልሳችን የገባነው።  
Dagmawit
Dagmawit Moges and Kassahun Seboqa Source: SBS Amharic
  


Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service