አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ በአውስትራሊያ ታላላቅ ከተሞች የሙዚቃ ስራውን በማቅረብ ላይ ይገኛል። በቆይታውም ሜልበርን በሚገኘውን የኤስ ቢ ኤስ ራድዮ ጣቢያ በመገኝት ከአማርኛው ዝግጅት ክፍል ጋር በሙዚቃ ስራዎቹ ዙሪያ ቆይታን አድርጓል። አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ በተለይ የሚታወቀው በኢትዮ ጃዝ የሙዚቃ ስልት ፈጣሪነት እና አባትነት ነው። እንደ እሱ አባባል ከሆነ " እኔ ራሴን ፈለጌ፤ ራሴን እንዴት አድረጌ ላግኝ ? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የቻልኩት በተለይ ኒውዮርክ ላይ ነው ማለት እችላለሁ። የሙዚቃ ቅኝቶቻችን በአምስት ድምጾች ላይ የተመሰረቱ ናቸው። በዚሀም ራሴን ለመፈለግ ራሴን ለመፍጠር ኢትዮ ጃዝ የሚል የሙዚቃ ሳይንስ ነው የፈጠርኩት። ይህ ሳይንስ አምስቱን ድምጾች ከአስራ ሁለቱ የአውሮፓውያን ድምጽ ጋር በመደባለቅ የተሰራ ነው ። ኢትዮ ጃዝ በአሁን ሰአት አለም ላይ የተወደደ፤ የተፈቀረ፤ ብዙ አድማጭ ተከታዮች ያለው የሙዚቃ ስልት ነው። እና እንደዚህ ሆኖ ነው እራሴን አግኝቼ የተጓዝኩት ማለት ነው። "
Share






